አሜሪካ ልዩ ወታደራዊ ኋይሏን ወደ ሶሪያ ስታስገባ በሶሪያ ጉዳይ ቬና ላይ ከስምምነት እየተደረሰ ነው::
የአሜሪካ ባለስልጣናት እንዳሉት የኦባማ አስተዳደር የሶሪያ ለውጥ ፈላጊ አማጽያንን በወታደራዊ ድጋፍ ለማጠናከር እና አይሲስ የተባለን አሸባሪ ለመዋጋት ልዩ ሃይሏን ወደ ሶሪያ መላኳን ተናግረዋል::ወደ50 የሚጠጉ የአሜሪካን ልዩ ሃይል አባላት ወደ ሶሪያ ያቀኑት የአሳድን መንግስት ተቃውመው መሳሪያ ያነሱ አማጽያንን ለማሰልጠን ለማማከር እና ለመርዳት ሲሆን ይህ አሜሪካ መሬት ወራዳ በሶሪያ ወታደራዊ ስራዎችን በይፋ ስትሰራ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ታውቋል::
የአለም ሃያላን ለሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት መፍትሄ ለመሻት በቬና ኦስትሪያ ታሪካዊ የተባለለትን ስብሰባ የተሰበሰቡ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በተሻለ ሁኔታ ከስምምነት ቢደርሱም የሶሪያው ፕረዚዳንት በሽር አልኣሳድ እጣ ፈንታ ላይ ከመግባባት ላይ መድረስ አልቻሉም::በዚሁ የሶሪያ ጉዳይ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የአሳድ ደጋፊ የሆነችው ኢራት ተሳትፋለች::