በስልጤ ዞን የሂጃብ ገፈፋውን በመቃወም በአደባባይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ተገለፀ::

Hamza Borana's photo.

በስልጤ ዞን በሁልባራግ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የሂጃብ ገፈፋውን በመቃወም በአደባባይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ተገለፀ

በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን የሂጃብ ገፈፋው ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በከተማው ህዝበ ሙስሊም እና በመንግስት ሃይሎች መካከል ግጭት እየተፈጠረ መሆኑ ታውቋል፡፡

በስልጤ ዞን የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሂጃብ ክልከላውን በመቃወም ተማሪዎቹ አድማ እየመቱ የሚገኝ ሲሆን የሂጃብ ክልከላው እስከሚቆም ድረስ ወደ ትምህርተ ቤት እንደማይሄዱ እያስታወቁ ይገኛሉ፡፡

በስልጤ ዞን በሁልባራግ ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው ኬራቴ በተሰኘው ከተማ ከቀናት በፊት በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን የጠየቁ ተማሪዎች እና ህፃናትን በሃይል በመደብደብ እና ጥይት በመተኮስ ለመበተን ጥረት መደረጉ ተዘግቧል፡፡

ተማሪዎች ላይ እየተወሰደ የሚገኘውን የሃይል እርምጃ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰላማዊ መንገድ የተቃወሙ ሲሆን የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ግን ህዝቡን በዱላ በመቀጥቀጥ መበተናቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡፡

በዛሬው ዕለትም በሁሌባራግ ወረዳ በሁልባራግ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሂጃባችሁን አውልቃችሁ ተማሩ መባሉን ተከትሎ ተማሪዎች ት/ ቤቱን ለቀው በመውጣት በከተማው አደባባይ ላይ መብታችን ይከበር ፣የሂጃብ ገፈፋው ይቁም ” የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ መዋቸው ተዘግቧል፡፡

ውረጥቱም በዛሬው ዕለት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ፖሊሶች ወረዳውን በመክበብ ሙስሊሙን ሲደበድቡ እንደበር ታውቋል፡፡ በዚኅ ድብደባም በርካቶች መጎዳታቸው የተዘገበ ሲሆን መንግስት የሃይል አማራጮችን መፍትሄ አድርጎ እየወሰደ እንደሚገኝ ተገልፆል፡፡
ፍትህ ራዲዬ / ጥቅምት 17/2008 ۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩

Hamza Borana's photo.

Hamza Borana's photo.
Hamza Borana's photo.