በትግራይ ክልል ለተከሰተዉ የድርቅ ኣደጋ ለመከላከል እየገባ ባለዉ የእርዳታ ስንዴ ለግል የዱቄት ፋብሪካ እየተሸጠ እንደሆነ ተሰማ።
በትግራይ ክልል ለተከሰተዉ የድርቅ ኣደጋ ለመከላከል እየገባ ባለዉ የእርዳታ ስንዴ ለግል የዱቄት ፋብሪካ እየተሸጠ እንደሆነ ተሰማ።

በዝናብ እጥረት ሳብያ በተከሰተዉ የድርቅ ኣደጋ በተለያዩ የክልሉ ኣከባቢዎች የረሃብ ኣደጋን እያሰከተለ ቢሆንም ለጋሽ ድርጅቶች ኣደጋዉ ለመከላከል እያስገባ ባለዉ የእርዳታ ስንዴ ለጭረት ከ250-300 ብር ለግል ዱቄት ፋብሪካዎች እየተሸጡ ሞሆናቸዉ መረጃዉ ያመላክታል።በትግራይ ክልል የኣደጋዉ ዕርዳታ እየደረሰ ያለዉ እስከ ኣሁን የሰዉን ህይወት ማለፍን ከጀመረ ወዲህ ዘግይቶ ቢሆንም ኣሁንም ቢሆን ከወዲሁ ለእንደዚህ ኣይነት የሙስና ተግባራትና ስርቆት ተጋልጧል።
የዕርዳታ ስንዴዉ በኣንድ በኩል ብሩ ለዓባይ ግድብ ይሆናል በሌላ በኩል ጎተራዎቹ ብሞምላታቸዉ ምክንያት ነዉ በሚል ኢ ምክንያታዊ ማታልያና ረቂቅ የሙስና መረብ ከውዲሁ በመንደፍ ስንዴዉ እየሸጡት ሞሆናቸዉ ገልጸዉልኛል። ይህ መርጃ ለማረጋገጥ በመቐለ ከተማ በሚገኙ የግል ዱቄት ፋብሪካዎች ዙርያ ተዘዋዉሬ የተመለከትኩት ሲሆን በለምለም የዱቄት ፋብሪካ ሁለት ተሳቢ መኪኖች ዛሬ 08/02/08 ዓም ሳይራገፉ በፋብሪካዉ ዉስጥ ቁመዉ ያየሁት ሲሆን ሌሎችም ወደ ኣከባቢዉ እየተጓዙ እንደሆኑም በመንገዱ ስመለስ ኣግኝቻችዋለሁኝይሁን እንጂ ይህ መረጃ በቂ መረጃ ነዉ ብየ ስለማልቋጨዉ ተጭማሪ መረጃ ለማግኘት በጠረት ላይ ነኝ። በኣሁኑ ወቅት ትግራይ በረቂቅ የሙስና መረብ ተከብባ እንደሆነች በግልጽ እየተነገረዉ ነዉ ::