የሻእቢያ መሪ በጭንቅላት እጢ እና ጉበት በሽታ ታመዋል::የኢትዮጵያ ነጻ አውጪዎች ቡድን አዲስ ስትራቴጂ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል

ኤርትራ በኢታማዦር ሹሟ እየተመራች ሲሆን የሻእቢያ መሪ መታመማቸውን ከአስመራ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ::ከሃገር ውጪ በሕክምና ላይ የሚገኙት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ እጅግ አደገኛ ሁኔታ ላይ በመሆናቸው ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል::በምትካቸው ኢታማጆር ሹሙ ጄኔራል ፊሊጶስ ቦታውን ይረከቡታል ተብሎ ይጠበቃል:: በአስመራ የነገሰውን ውጥረት አደባባይ እንዳይወጣ ለማርገብ በጄኔራል ፊሊጶስ የሚመራ የደህንነት እና ስለላ ቡድን ተደራጅቷል:: የአቶ እሳያስ አፍወርቂም ስልጣን መልቀቅ ተከትሎ በአስመራ ለውጥ ይኖራል የሚል ተስፋ ያለ ሲሆን ስልጣኑን ይረከባሉ የሚባሉት ወታደራዊ ጄኔራል ዘመናዊ እና ከምእራባውያን ጋር መልካም ግንኙነትን ይፈጥራሉ ተብሎ ይነገራል::ይህ በእንዲህ እንዳለ አስመራ የሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ አውጪዎች ቡድን ጉዳይ ጸጥ እረጭ እንዳለ ነው::አዲስ ስትራቴጂ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል:: በቅርቡ ከዱባይ ተዝናንተው የተመለሱት የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪዎች በጭንቀት እና በድብርት ውስጥ ስለሆኑ እንዲሁም በኤርትራው ትግል ተስፋ ስለቆረጡ እንደማያዋጣ ስለተረዱት በቅርቡ ከአስመራ ተጠቃለው ከወጡ በኋላ በአዲስ ስትራቴጂ ከሕዝብ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና 25 የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት በሽራሮ በኩል ለወያኔ እጃቸውን መስጠታቸው ሲታወቅ ወያኔ በቀጣይነት የዶክመንተሪውን ድራማ ለስራት በዝግጅት ላይ መሆኑን ታውቄል::