“ወያኔዎችን አጥኗቸው፣ እወቋቸው“ ሙሉጌታ ሉሌ

ሙሉጌታ ሉሌ / Mulugeta Luleበልጅግ ዓሊ

"ደግ ደጉን ስናጣ፣ ኀዘኑ መረረ

ሞት አምላኩ ከድቶት፣ ገሎት በነበረ።"

- የሠፈራችን ሙሾ አውራጅ

እነሆ ጋሼ ሙሉጌታ ዐረፈ። ከዚህ ምስቅልቅሉና ቅጥ አምባሩ ከወጣ ዓለም በአካል ተለየ። ጋሼ ሙሉጌታ ከእንግዲህ የሀገሩን አፈር በሞቱ እንኳ ላይቀምስ ነው። ዛሬ የሰው ሀገር አፈር ለብሶ በዝምታ ማሸለቡን መርጧል። ሀገሩን እንደናፈቀ የተለያት ቢሆንም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር ትምህርት ሰጥቶን አልፏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

6 Comments on ““ወያኔዎችን አጥኗቸው፣ እወቋቸው“ ሙሉጌታ ሉሌ”

  1. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    ወያኔ ካበደ ሠነበተኮ

  2. ምን ኣንድ የኢሰፓ ቱልቱላ ሞተና ልናዝን፧
    ስንት ምርጦችን ያስጨረሰ ደብል ፌስ ክፍት ኣፍ ኣይደል

  3. I know THIS OLD MAN is the member of dictators there is no any space in Ethiopia know be aware diaspora.

  4. ጋሼ ሙሉጌታ ሉሌን በዐይኔ አይቼው ብጣቂ የአማተር ግጥሜን የሰጠሁት ካሳንቺስ ከፍቶት ወደነበረው ጽህፈት ቤት ሄጄ ነበር፤በዚያች ቀን የሰጠኝ አጭር የቃል ምክር፣”በአሁኑ ዕድሜህ ከምትጽፍ ብታነብ ይሻልሃል”ያለኝ ነውና ይሄው ዕድሜዬን ሙሉ የመጽሐፍ ቀበኛ ሆኜ የሕሊና ተገዥ አድርጎኛል።ለዚህም ነው የጉጅሌውን ሕሊና ቢስነት ለመዋጋት የቆረጥኩት።
    አንባቢዎቼ ኢትዮጵያውያን:-ጋሼ ሙሉጌታ “ወያኔዎችን አጥኗቸው ፣ እወቋቸው “ማለቱ እንድናመርና ኢትዮጵያን እንድናድን” ነው::ቤልጅግ አሊም ይህንኑ ተጭኖ ያስረገጠን ማስመሰሉን እንድናቆም ነው:-ስለብዕሩ ክብረት ይስጥልን::
    እኔማ ከአገር ለቅቄ ለመውጣት ስወስን ነው ጉጅሌን ከትኋን የከፋ ደም መጣጭ መሆኑን አጣርቼ የመገለ የሚመስል አክታዬን የተፋሁበት፤በደም ያበጠ ዘረኛ ባሕርዩን አንጀቱ ውስጥ ድረስ ገብቼ የዛሬ ሃያ ዓመት በማየቴ።እስኪ በግጥሜ ልሳን የተሰማኝ አንቡልኝ፤
    ያቺን ቅማል ትኋኗን
    “ጉጅሌን” አግኙ።
    (0)(0)(0)(0)
    እባካችሁ ወገኔ ዛሬም አትሞኙ፤
    ቅድሚያ ያቺን ቅማል ትኋኗን አግኙ።
    ሺህ ቦታ መቶ ጥግ በየጉራንጉሩ፤
    ማከክ መሞዠቁ ማልቀስ መቆፈሩ፤
    ለሰይጣን ደንግጦ ሬሳ መቁጠሩ፤
    መፍትሔ ባይሆንም እንደው ለጅምሩ፤
    እንድንነጋገር ከልብ ግን አምርሩ።
    የምር ካዘናችሁ በሰይጣኖች ድርጊት፤
    በመንፈ በሥጋ ተዘጋጁ በፊት።
    በመንፈስ ፀልዩ ፅሙና ስገዱ፤
    በሥጋዊ ደግሞ የሙሴን ውደዱ።
    ሙሴ ከባርነት ሕዝቡን እንዳወጣ፤
    ዘራፊ ሰው ገዳይ ከያለበት መጣ።
    በልመና እንዳይሆን ቀድሞ ስላወቀም፤
    ጠላትን ለመግደል ከእግዜር አልጠበቀም።
    የመጋደላችን ረቂቅ ሚሥጥሩ፤
    በሥጋም በመንፈስ ይሁን ከጅምሩ።
    እናማ ዕወቁት ለጠላት አትተኙ፤
    ያቺን ቅማል ትኋኗን
    ጉጅሌን አግኙ።
    ሁላችንም ብናውቅ ሰይጣኖች እንዳሉ፤
    ከጉያችን ሆነው እንደሚያቀብሉ፤
    እኛ ስንናገር እየተከተሉ፤
    አይን አውጥተው ደግሞ እንደ እኛ ያነባሉ፥፥
    በነሱ ምክንያት እኛን ያስገድሉ፤
    መሆኑንም ብናውቅ ተደብቀው አሉ።
    ገና ምን፡ተነካ እንደተነገረን፤
    “መራራው ይመጣል”በይደር የቀረን።
    ማነው ከእግዜር በልጦ አዋቂ፡ነኝ የሚል፤
    ሰሚ አገኘሁ ብሎ ሕዝብን የሚያታልል፧
    ከምር ቅማል ትኋን ዛሬ ካልተገደሉ፤
    ማሳከክ አይደለም በዝተው ይገድላሉ።
    ምን ያደርጋል ለእኛ ሬሳን መቁጠሩ፤
    ስንት ኢትዮጵያዊ አሉ በየትም የቀሩ።
    አልገባንም ቋንቋው፧ ሰበብ ምክንያቱ፧
    ጠፋን ወይ መንገዱ የኢትዮጵያዊነቱ፧
    ወይስ ከድግምቱ ሳንፈታ የቀረን፧
    በስልጣን በገንዘብ ትናንት እንዳሰረን፤
    ሞተናል ወይ ቆመን ጎሳ እንደጠፈረን፧
    «ወቸገል ዜናዊ»እንደዘረዘረን።
    እንግዲያስ ሳንሞኝ የዛሬን አትቀሙኝ፤
    መፍትሔ የሚሆን የደም ቃሌን ስሙኝ።
    ዕወቁት ጠላትን ዛሬም አትተኙ፤
    በዕርኩስ የተያዘ ይላል ያ “ሰው ሞኙ።”
    እናም ከራሳችን በ«ማን ነኝ፧» እንጀምር፤
    ኋላም ለመታገል እንዘጋጅ የምር።
    ቅድሚያ ለመጋፈጥ ከጠላታችንም ጋር፤
    በተናጠል ሳይሆን እ-ን-ፈ-ል-ግ አጋር።
    ተስፋና መልካሙን ግና የምትመኙ፤
    ያቺን ቅማል ትኋኗን
    ጉጅሌን አግኙ።

  5. Some people instead of comment they chose insulting.
    Please you can support woyane but give some clarification how you support woyane and stop insulted like you don’t have brain.

  6. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    ሁሉም የወያኔ መሪዎች መሀይም ናቸው ሀገር ቤታችን እንደገቡ ሁሉም ሜክሢኮ የሚገኘው አጋዚያን ትምህርት ቤት እሥከ 8ተኛ ተከታትለው ቀሪውን በተጭበረበረ የትምህርት ማሥረጃ ዛሬ ዶክተር ነን ሢሉ እየሠማን እያየን ነው ትንሽ መምህራንን አትፈሩም ሥማቸውን በቅጡ እንኳን አያውቁም።

    የሌባ የባንዳ ዝርያ ወያኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*