ኢህአዴግ በሚጠራው መድረክ አለመገኘት ማንን ይጠቅማል? ግርማ ሠይፉ ማሩ
ቅጥ አንባሩ የጠፋው የኢትዮጵያችን ፖለቲካ በዋነኝነት የሚጎድለው ልክ ያልሆነን ነገር ልክ አይደለም ማለት ያለመቻል ነው፡፡ በግል አስተያየት ልክ አይደለም ብሎ መቆም ደግሞ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ የተሳሳተ ውሳኔ ባለቤቶች በድጋሚ ጥፋታቸውን በጥፋት ለማረም ሌላ ስህተት ይደግማሉ፡፡ አሰተያየትን በአሰተያየት ለመመለስ ይከብዳቸዋል፡፡ የዚህ ደግሞ ዋነኛው ሰለባ የተቃዋሚው ጎራ ነው፡፡ ለነገሩ አሁን ይህ ነው የሚባል ተቃዋሚ አለ ባይባልም፤ ያሉትም ቢሆኑ ከልምድ የሚማሩ ዓይነት ሆነው አልተገኙም፡፡
ለዛሬ ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ አንድ ሰሙ “የአንዳርጋቸው ፅጌ ብርሃን” በሚል የብዕር ሰም የሚከተለውን መልዕክት በፌስ ቡክ ገፄ የውስጥ መልዕክት ማስቀመጫ
“ግርማ ካሳ (ልብ በሉ እኔ ግርማ ሠይፉ ነኝ) ወረድክብኝ በጣም። ተፈጭቶ ተቦክቶ ተጋግሮ ሊበላ የቀረበውን ነገር ድጋሚ ወፍጮ ቤት ይሂድ ብለክ እየተከራከርክ ነው። 24 አመት ሲያታልል የኖርን መንግስት ዛሬ 25ኛው አመት ላይ ሆነክም እንዴት አልገባክም? ስንት አመት ነው የሚፈጀው እንዳንት አይነት ሰዎችን ለማብሰል? ተወያየተክ ምን ታተርፋለክ ? ወያኔ ተቃዋሚዎችን የሚፈልገው ለተራ ፕሮፖጋንዳው ሊጠቀምባቸው እንጂ ለነሱ ሀሳብ ጆሮ ለመስጠት አደለም። መንግስት እራሱ ያወጣውን ህግ ጥሶ ያሰራቸውን የፓርቲ አባሎችን ለማስፈታት ከወያኔ ጋር ስብሰባ መቀመጥ አያስፈልግም። እንዲ የምታስብ ከሆነ ከአልም ሁሉ ተለይተክ ከሀይለማርያም ደሳለኝ ብቻ የተሻልክ ጅላጅል ነክ ማለት ነው። ወያኔ ለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጻፈውን ድብዳቤ ልብ ብለክ አንብበከዋል ? እንዲ የሚል አርፍተ ነገር አለበት። “በሀገራችን የሚገኙ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች “እንደ መላው የሀገራችን ህዝቦች ” እያለ ይቀጥላል። ሲጀመር ወያኔ እነዚ ፓርቲ ብሎ የሚያውቃቸው ድርጅቶች ከህዝብ ተለይተው ያሉ እና የህዝብ ድጋፍ የሌላቸው አርጎ ነው የጠራቸው። ፀረ ህዝብ አርጎ ነው የሚስላቸው። አንደ ህዝብ አካል አርጎ አይቆጥራቸውም አያከብራቸውም። አንዳንተ ዓይነት አሟሟቂ ሰው ነው ወያኔ የሚፈልገው።ኢቢሲን አሟሟቂ”
የሚል መልዕክት አስቀመጠልኝ፡፡
መልዕክቱ የተፃፋው በዚህ ጉዳይ አስተያየት ለሰጠው ወዳጄ ግርማ ካሣ ይመስላል ነገር ግን የተላከው ለእኔ በእኔ አድርሻ እና እኔን በዓይነ ልቦናው እየሳለ እንደሆነ ያስታውቃል፡፡ በእኔ እይታ ደግሞ የግርማ ካሣን ሃሳብ መደገፍ ብቻ ሳይሆን በግል ለደወሉሉኝ አቋሜን ገልጬ ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ ግን ሚዲያ ላይ ወጥቶ አስተያየት መስጠት ብፈልግም፤ ብዙ ምቾት አልተሰማኝም ነበር፡፡ ለማነኛው የዚህ አሰተያየት ሰጪን ሃሳብ መነሻ አድርጌ የግሌን አስተያየት ላቅርብ፡፡
በመጀመሪያ ማነኛውም ግብዣ ላይ የተጠራ ሰው ግብዣ የሚሄደው በመከባበር ሰሜት መሆን አለበት፡፡ ጠሪ አክባሪ በሚል እንጂ ግብዣው ላይ ምን ድግስ አለ በሚል መሆን የለበትም፡፡ በእኔ እምነት ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራዊ አጀንዳ ላይ ከዚህ በፊት ጥሪ ተደርጎላቸው የማያውቁ የፖለቲካ ፓርቲውች መድረክ፣ ሰማያዊ እና መኢህአድ ግብዣ ተደርጎላቸዋል፡፡ ለምሳሌ በመጀመሪያው የአምስት ዓመት ዕድገትና ትራንሰፎርሜሸን ዕቅድ እና በአባይ ግድብ ወቅት ጥሪ ስለ አልተደረገላቸው አልተጠራንም ሃሳባችንን መስጠት እና የጋራ ማድረግ አልቻልንም ሲባል ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የፖለቲካ ምዕዳሩም ሆነ አጠቃላይ ሀገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ተመሳሳይ ነበር፡፡ በዛን ጊዜ ተቃዋሚዎች አልተጠራንም ሲሉ የነበረው ተጠርተው ለመቅረት አይመስለኝም፡፡ ተገኝተው ሃሳባቸውን ለማካፈል ይመስለኛል፡፡
በእኔ እምነት አሁን በተደረገው ጥሪ መስረት ከላይ ሰማቸውን የጠቀስኩት ፓርቲዎች ተገኝተው የሚከተለውን ማከናወን ይችሉ ነበር፡፡ መጀመሪያ ያለፈው አምስት ዓመት ክንውን ሲቀርብ ከመነሻው ጀምሮ በጋራ ከተቃዋሚዎች ጋር በጋራ ለመስራት መንግሰት እርምጃ ባለመውሰዱ የእቅዱ ዋና ዋና ምሶሶ የሆኑት ተግባራት ያለመሳካታቸውን በተጨባጭ ማስረጃ ለማስረዳት እድሉን ሊጠቀሙበት ይችሉ ነበር፡፡ ለምሳሌ የባቡር ዝርጋታ ከታቀደው 30 ከመቶ ያለመሰራቱ፣ በኤሌትሪክ ሀይል በተመሳሳይ 20 ከመቶ እንኳን ያለመሳካቱ፤ በመንገድ በውጭ ንግድ፣ በዋጋ ማረጋጋት፣ በግብርና በተለይ በሰፋፊ እርሻ ወዘተ.. ያሉትን መሰረታዊ ችግሮች በማሳየት ለዚህ ዋነኛው ችግር በጋራ በመስራት ሊገኝ የሚችለውን ሀገራዊ ሀይል ወደ ጎን ማድረጋቸውን ለህዝብ ይፋ ማድረጊያ መድረክ ይሆን ነበር፡፡ በተለይ የአባይ ግድብን ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ መጠቀሚያ እንዲሆን በማድረጉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሊያደርጉ የሚችሉት ከፍተኛ አሰተዋፅኦ መገደቡን ለመናገር ከዚህ የተሻለ ትክክለኛ መድረክ የሚያገኙ አይመስለኝም፡፡ ይህንን መድረክ ለመጠቀም ባለመቻላቸው ትልቅ የፖለቲካ ኪሣራ ይመስለኛል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ገዢው ፓርቲ እራሱ ያመነውን የመልካም አስተዳደር መፍቻው ቁልፍ መንገድ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ እና በተለይ ደግሞ የሚዲያዎች ተሳትፎ መኖር ተዓማኒነት የሚጣልባቸው የፍትህ ስርዓት መሆኑን በሰብሰባው በሚፈጠሩ አጋጣሚዎች ሁሉ በማንሳት ዕቅዱ ያልተሳካው ይልቁንም ሙስና የተንሰራፋው ስርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኘኞችና አምደኞች በመታሰራቸው፣ እምነት የሚጣልበት የፍትህ ስርዓት ባለመኖሩ እንደሆነ አጋጣሚውን መጠቅም ይቻል ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዝግጅት አድርገው መሳተፍ እንጂ አድማ አድርጎ ከግብዣ በመቅረት ውጤት የሚገኝ አይመስለኝም፡፡ ይህ ትልቅ ሰህተት ይመስለኛል፡፡
ከዚህ ውይይት በማስከተል “የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም” በሚል ተረት ከገዢው ፓርቲ ጋር ተመራርቆ ለመውጣት ሳይሆን በቀጣይ ዕቅድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ ሀገራዊ አጀንዳዎች በምን መልክና ደረጃ ስንሳተፍ ይህ ዕቅድ ተግባራዊ ይሆናል በሚል መነሻነት የድርጊት መርዓ ግብር በመንደፍ የጋራ ኮሚቴ አቋቈሞ መውጣት፣ በተለይ የፖለቲካ ምዕዳሩ ለማስፋት የሚቻልበት መንገድ መቀየስ ሊሞከር የሚገባው ትልቅ ስራ ነበር፡፡ ይህ ከገዢው ፓርቲ ባህሪ አንፃር ተቀባይነት ባያገኝ እንኳን እንቢተኝነቱን ለማጋለጥ ይረዳ ነበር፡፡ እንደ ፓርቲ ሰርተፊኬት ይዞ ዓመት ከመቁጠር በዘለለ መንግሰት በተገኘበት ሁሉ እየተገኙ ድምፅ ማሰማት (ባይሰሙም መጮኽ) ግዴታቸው ነበር የሚል የግል አቋም አለኝ፡፡
እውነቱን ለመናገር በቁጥር እስከ ሃያ የሚደርሱ የፓርቲ አባላትን (ለምሳሌ ሶስቱ ፓርቲዎች 60 አባላትን) በአንድ መድረክ ላይ እንዲገኙ የተሰጠን እድል ያለመጠቀምን ያክል ደካማ ውሳኔ አይታየኝም፡፡ እያንዳንዳቸው ሁለት ደቂቃ መልእክት ቢያስተላልፉ የሁለት ሰዓት መልዕክት በመንግሰት ጆሮ ላይ ማስቀመጥ ይቻል ነበር፡፡ እነዚህን አጋጣሚዎች በእስር የሚማቅቁ ጓዶቻችንን በማንሳት ልንዘክራቸው ይገባ ነበር፡፡ አሸባሪ ያሏቸውን “ጀግኖች” ብለን ልናወደስ የምንችልበት መድረክ ያለመጠቀም በምን መመዘኛ ልክ እንደሚሆን አይታየኝም፡፡
ገዢው ፓርቲ ከአሁን በኋላ ለማነኛውም ዓይነት ውይይት ሳይጠራ ዳተኛ ቢሆን ሰበብ አግኝቷል፡፡ ቢጠሩም አይገኙም ይልቁንም በሚጠሩበት መድረክ ከመገኘት ይልቅ ውጪ ሆነው መግለጫ በማውጣት ላይ ይገኛሉ ብሎ ለሀጋሮቹ ማስረጃ ያቀርባል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከኢህዴግ መንግስት ባልተናነሰ ካድሬ የሆኑ የአሜሪካን እና አውሮፓ ህብረት ድጋፍ ሰጪዎች ይህን ለመስማት እና ለማመን ብዙ አይቸገሩም፡፡
በእኔ አረዳድ ፓርቲዎቹ በግብዣው ላይ ተገኝተው በምን ጉዳይ አተኩረው እንደሚናገሩ እንዴት አድርገው የፖለቲካ ጥቅም እንደሚያገኙበት መካሪ አላገኙም፣ በውስጥም በቅጡ አልመከሩበትም፡፡ የሚያሳዝነው እነዚህ ፓርቲዎች የአሜሪካ ኤምባሲ ለስዕል ኤግዚቢሽን ምረቃ ቢጠራቸው በግብዣው ላይ ይገኛሉ፡፡ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባል ሊያነጋግራችሁ ይፈልጋል ቢባሉ ይገኛሉ፡፡ መገኘት ብቻ ሳይሆን አነጋገሩን ብለው ዜና ይሰራሉ፡፡ እንግዲህ አንባገነኑ ኢህአዴግ ዲሞክራት እሰኪሆን ጠብቀው ለመወያየት ከሆነ ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡ ባለፈው ፕሬዝዳንት ኦባማ ጉብኝት ሲያደርጉ ለግንኙነት በሚመቸው የእራት ግብዣ ላይ ላለመገኝት ወስነው በብዙ ሜትር ርቀት በቴሌቪዥን በተሻለ ለመከታተል በሚቻልበት የአዳራሽ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ሲወስኑ ዝም ማለታችን አበጃችሁ ያልን የመሰላቸው መሪዎች፤ ይህንንም ግብዣ ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል አለመቻላቸውን ዝም ማለት ተገቢ አይደለም ለማለት ሲባል የቀረበ አስተያየት ነው፡፡ በእኔ እምነት በሰላማዊ ትግል በሀገር ውስጥ ለመንቀሳቀስ የወሰነ ማንኛውም አካል መንግሰትን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እያገኙ መልዕክት ማስተላለፍ ተገቢ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ እና መንግሰት በሚጠሩት ማንኛውም ስብሰባ ላይ ላለመገኘት መወሰን የሚጠቅመው ገዢውን ፓርቲ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ሃሣብ ያለው በመቅረት የሚገኘውን ጥቅም ቢያስረዳኝ፣ በተለይ አሁን በተደረገው የሁለተኛው የእድገት እና ትራነስፎርሜሽን እቅድ ለመወያየት በተደረገው ጥሪ ላይ ያለመሳተፍ ያስገኘውን ጥቅም ለሚያስረዳኝ ለመማር ዝግጁ መሆኔን እገልፃለሁ፡፡ በደፈናው ገዢውን ፓርቲ እውቅና መንፈግ የሚል መልስ ግን አልቀበልም፡፡ በሀገር ውስጥ ሆኖ በዚሁ መንግሰት ስር እየተዳደሩ እውቅና መንፈግ የሚባል ፖለቲካ አይገባኝም፡፡
ቸር ይግጠመን!!!!
Mr.Girma seifu, the veteran politician, sounds like a planted wuyane erand boy. He thinks he is the only person who can democratize wuyane. Tagadalai Girma, you are completely wrong. Boycotting is also one of the peaceful method of passing message to the dctators. You are dead wrong. You can’t continue misleading our people anymore. You are becoming a collaborator. You don’t deserve thanks now.
አቶ ግርማ! ምንድነው የተማርከው? ፖለቲካውን ተወውና ለምን ስራህን እየሰራህ አትኖርም? እንደማይህ በአምባሰል ቅኝት ባቲ ለመዝፈን እያሰብክ ነው። አንተ በምዕራባዊያን (የሰለጠነው ዓለም) ፖለቲከኞችን አስተሳሰብ ይዘህ በአፍሪካ ለዚያውም በወያኔ ማጀት ምንም ፖለቲካ ልትሰራ አትችልም። አሁንም ከወያኔ ጋር ለመሀጋገር ታስባለህ? ለምን? ምን ለማግኘት ምን ለመለወጥ? ከማንም በላይ ወያኔ ሊለወጥ ያማይችል! ተቃዋሚን እንደ ጠላት የማየት ልምዳቸው ሊጠፋ የማይችል መሆኑን ታውቃለህ። ታዲያ ተቃዋሚዎች ጥሪውን ተቀብለው ለምን አልሄዱም ብለህ መጠየቅህ ምን የሚሉት አስተሳሰብ ነው? ለኢህአዴግ መንግስት እውቅና መንፈግ አልሻም ስትል ምን ማለትህ ነው? ምርጫውም የአንድነት አፈራረስም ተገቢ ነበር ማለትህ አይደለምን? ንዙ ጥያቄ ነበረኝ ምን ዋጋ አለው… ለማንኛው የተመስገን ደሳለኝ ” የፈራ ይመለስ” እንዳለው፤ ከፈራህ ተመለስ እንጂ ስለ 5 ዓመት ትራንስፎርሜሽን እቅድ ምናምን እያል አታድክመን። 5 ዓመት በተቃዋሚ ስም ምክር ቤት ተቀምጠህ የፈየድከው ነገር አለን? ምንም ..! ተው ብዙ አታናግረን… አርፈህ ስራህን ስራ
አንተ አረጓዴ መነጽር ነው ያደረከው እንደ ጋብሮብ ፈረሶች (ደረቅ ሳር አልበላ ሲሉ)
ወያኔ ይወገድ
ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት እያደገች ነው:እድገቷም ተአምራዊ ነው:
ወያኔ ይወገዳል
የደንቆሮ ነገር መልሶ መልሶ ነው(A statement from stupid TPLF cadre-ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻ).
[Reply]
ማድጋ ሰባሪና የአራዳ ልጅ ሰምና ወርቅ ናቸው:እናት ከመሳደብ ወደ አስመሳይነት ብቅ ማለቱ ዋጋ የለውም:እየነካኩ ለማጥመድ መሞከርም የትም አያደርስም:የሳይበሩ ጨዋታ ተሟሙቆ ይቀጥላል!!!
Gulicha!!!!
እኔም ወያኔም አብረን ማበዳችን ነው ዘንድሮ እንደ እብደቴ ከሆነ የመለሥን ሬሣ ላቃጥለው እንዴ?
This article should read ” e-adeg bemiteraw medrek megegnet manin yetekmal?” The people of benefit anything for a political organization that told us it won it all. You see, lukewarm politician are dangerous because they couldn’t make up their minds. This political organization declared war on Ethiopia and Ethiopians long time ago. It is shooting at us while we are getting shot. Now it wants us to seat with it to affirm our degradation and humiliation. Hell no!
Correction ” of Ethiopa will not benifit anything “
ውነትክን አቶ ግርማ መወያየት ጥሩ ነው:
ተቃዋሚወች መወያየት ነበረባቸው:ሰማዊና መድረክ ትልቅ ጥፋት አጥፍተዋል:ለነገሩ ከአፍራሽ ምን ይጠበቃል:
Ayy andd le natu, antem ke weyane majet kemeskina magonbes jemerk, lemehonu be ante dirjt ena be 2007 mircha yeteseraw sira bicha enkua erm endtaweta ayarghm….
Ayy andd le natu, antem ke majet kemeskina magonbes jemerk, le mehonu be drjith lay yeteserawna ye mircha 2007 wutet bicha enkua erm endtaweta ayeregmih, wey ende lidetu be 3 nga menged eyakobekobk neww, ygermal seww yetun yahl kibr endemisetachuna tesfa endemyadergbachhu atawkum…
How ?
How is woyane going to be removed any idea?? I am willing to learn.
It is really sad how this girma seifu has regressed to become a traitor overnight and has fully engaged in attacking the legal oposition parties who are doing their best under the difficult circumstances. Has girma been really an honest oposition or a wuysne planted individual?
He has become the carbon copy of Ato Lidetu Ayalew. I think,he will be appointed very soon to lead the FAKE wuyane oposition group.
አቶ ግርማ ሰይፉን እደግፋለሁ።
ምክንያቱም ስንት ጊዜ ነው፣ ተቃዋሚ ድርጅቶች ኢህአዴግን ጥሪ አድርገንለት እንዲያነጋግረን እምቢ አለን እያሉ ስሞታ ሲያሰሙ የነበረው። ስለዚህ አሁን ጠሪው ኢህአዴግ ስለሆነ ነው ለመገኘት ያልፈለጉት? በኔ ዕምነት እንኳንና ተጠርተህ፣ ሳትጠራ ስትቀርም በዕውነት መፍትሔ ፈላጊዎች ከሆንን ማለቴ ነው፣ ተረስቼ ሊሆን ይችላል እንጂ ከጥሪ አልቀርም በማለት ሄዶ ሁኔታውን ማስረዳት ይቻል ይመስለኛል።
“ቂጥ ገልቦ ራስ ክንንብ” ይላል የአገሬ ሰው፤ ትዕቢትና ኩራት ለተቸገረ ሰው መፍትሄ አይሆንም።
የናቀ ወደቀ እንደሚባለው፣ ስትንቁ ስትንቁ፣ አንድም ቁም ነገር ሳታደርጉ ጊዜው እየሄደባችሁ መሆኑን ማወቅ አለባች ሁ።
ይህን ስል ያለው አስተዳደር ምሉዕ በኩለሄ ነውና አርፋችሁ ተቀመጡ ማለቴ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ። እርሱማ ጤና ቢሆን ሁላችንም በሰላም አርፈን በተቀመጥን ነበር።
ሁሌ በመነጋገር ነው መፍትሄ የሚገኘውና አሁንም አልረፈደም ሞክሩ ግዴለም።
ከዚያም በላይ መፍትሄው ከእግዜር ዘንድ ነውና እግዚአብሄር ዕርቀ ሰላሙን ያምጣልን። ሁላችንንም ሰፊ ልቦና ይስጠን። የውጭ አማካሪዎችን ከምንፈልግ፣ እርስ በርስ መነጋገር ነው የሚበጀን። አማካሪ ተብዬዎች በየቦታው ገብተው እያተራመሱ እንጅ መፍትሄ ሲያመጡ አልታዩምና አደራ እናስተውል።
Mr. Girma ,GOOD Bless you,totally I’m agree what you said.I understand EPRDF has many problems,but when you get the invitation paper you have to go for different reasons.1-Either you happy or not EPRDF become government of ETHIOPIA,so you have to respect the”government”.Attention I didn’t say EPRDF if you know politics you have to go.Why GINBOT-7 went ERTRIA?. Shabiya is good for OUR country? .To me you are loser.2_OK you didn’t go the meeting What EPRDF Loos?.
ምነው አቶ ግርማ – አሁንም የወያኔን ተንኮል አልተረዱትም ማለት ነው? መድረክና ሰማያዊ የወሰዱትን አቋም አለመደገፍ መብትዎ መሆኑን እገነዘባለሁ። የነሱን ምክንያት ለመረዳትም የሚከብድዎት አይመስለኝም ነበር። ዕውነት የተሰጣቸውን እድል ተጠቅመው ፋይዳ ያለው ነገር ይገኛል ብለው ያስባሉ? አዳምጡኝና አጨብጭቡልኝ ከማለት በቀር የሌሎችን ሐሳብ የሚሰማ ድርጅት ነው እንዴ ኢሕአዴግ? “እምቢ አንተ በዋልክበት አልውልም” ማለት እኮ የሰላማዊ ትግል አካል ነው። በበቀደሙ ምርጫ ምክያት ያሰራቸው፤ የገደላቸው፤ ከሥራ ያባረራቸው ወዘተ ሰዎች ጩኸትና ደም ምን ጊዜ ተረስቶ ነው ይሄ ሁሉ ሽር ጉድ? ስብሰባው ላይ ተገኝተው የሚያቀርቡት ሐሳብ ሰሚ ያገኛል ወይም በቲቪ/ሬዲዮ ይተላለፍና አገር ይሰማዋል ብለው ማሰበዎ የሚያስተዛዝብ ነው። ወያኔን አላወቁትም!! ወይም አውቀው እረስተውታል።