ቶሮንቶ የመጪው አመት 2016 በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ፌስትቫል ታስተናግዳለች::

የካናዳዋ ቶሮንቶ ከተማ የመጪውን አመት 2016 በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእግርኳስ ፌስትቫል እንደምታዘጋጅ
ESFNA አስታወቀ::ከአስረአመስት አመት በኋላ የቶሮንቶ ከተማ ይህን ፌስትቫል ስታዘጋጅ የመጀመሪያዋ ሲሆን በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ማህበር ደስታውን ገልጾ በቶሮንቶ ኢትዮጵያውን ኩራት እንደሚሰማው ተናግሯል::
ማንኛውንም የጉዞ እና የፕሮግራሙን መረጃ እንዲሁም አስፈላጊ ጉዳዮችን ከማህበሩ ማግኘት እንደሚቻል እና ማህበሩም በየጊዜው እንደሚያስታውን በማስታወቂያው ገልጿል::