ወያኔ የሻዕቢያ ጉዳይ ፈጻሚና ተላላኪ ነው – ተጠያቂነት ይኑር በአገር አይቀለድ፡፡ – ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ቁስለት ነው
የእስካሁኑ ሳያንስ አሁንም ይጨፈርብን? – (ከኢትዮጵያ ልጅ)
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን) የኤርትራ ቴሌቪዥን ሆነ እንዴ? ያስባለኝን ጥያቄ እንዳነሳ ያደረገኝ በነሐሴ መጨረሻና በጳጉሜን ወራት በተለያዩ ቀናት ደጋግሞ የኤርትራ ስደተኞች በስደት በሰፈሩበት ቦታ
ላይ የነፃነት ትግል የጀመሩበትን 54ኛ ዓመት በዓል በኢትዮጵያ ምድር እየደለቁና እየጨፈሩ ሲያከበሩ የነበረውን ጭፈራ እንደ ቀዳሚ የዕለቱ ታላቅ ዜና ሲያቀርብ በቁጭት በመመልከቴ ነው፡፡ ይኼ ቴሌቪዥን ጣቢያ የማን ነው? ብዬ እራሴን ጠየቁኩ፡፡
የቴሌቪዥን ጣቢያችን የጭፈራውን ዜና ሲያቀርብ የቀረው ነገር ቢኖር ኤርትራውያኑና የኢሕአዴግ መሪዎች እንደሚለፍፉት ከኢትዮጵያ የባርነትና የቅኝ ተገዥነት ነፃ ለመውጣት ኤርትራውያን ትግል የጀመሩበትን 54ኛ ዓመት አከበሩ በማለት እንኳን ደስ ያላችሁ ብሎ መለፈፍ ነበር፡፡
ከቁጭቴ በመነሳት ለእናት ኢትዮጵያ ክብር የሚያስብና የሚቆረቆር መንግሥት የለም ወይ? ብያለሁ፡፡
ከዚህ በፊት ሻዕቢያ ኤርትራን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ድረስ፤
-የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ሰጠናቸው እያሉ የቀለዱብን፣
-በሪፈረንደሙ ጊዜ በራሳችን ምድር በግልጽ የጨፈሩብን፣
-ከነፃነት በኋላ በመጀመርያዎቹ ሁለትና ሦስት ዓመታት የአዲስ አበባን የቀበሌ አመራር ይዘው የቦረቁብን፣
-የወያኔ መንግሥት ሆነ ብሎ ስላሞላቀቃቸው እኛ ኢትዮጵያውያን ሁለተኛ ዜጋ ኤርትራውያኖች ግን አንደኛ ዜጋና ባለመብት የሆኑበት፣
-በየመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እስከ ሚኒስትርነትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ ቁልፍ ቦታዎች የሰጠናቸው፣
-በ1983 ዓ.ም. ሻዕቢያ ከወያኔ ጋር በመሆን አዲስ አበባ ሲገቡ ጎተራ አካባቢ የነበረውን የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በማፈንዳትና በማቃጠል በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ሊያደርሱ የነበረውን ስቃይ፣
-በኢትዮ የኤርትራ ጦርነት የተከፈለው የጀግኞች ልጆቻችን መስዋዕትነት፣
-በመንግሥታችን የኢትዮጵያዊነት ስሜት ማጣት ኤርትራውያን የፈለጉትን መረጃና ሰነድ ከአገራችን እንዲወስዱ የተደረገው ተባባሪነት፣
-ኤርትራ የግላችን ኢትዮጵያ የጋራችን (የሁላችን) ተብሎ የተቀለደብን፣
-ኤርትራውያን ሥልጡኖች ኢትዮጵያዊያን ፈሪና ኋላ ቀሮች ተብለን የተሰለቀብን፣
ሳያንስና ሳይረሳ አሁን በራሳችን ቴሌቪዥን ጣቢያ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል 54ኛውን የነፃነት ትግል የጀመርንበት መታሰቢያ ክብረ በዓል ብለው ይጨፍሩብን እንዴ? እጅግ የሚያሳዝንና የሚያቆስል ድርጊት ብቻም ሳይሆን ወንጀልም ነው፡፡ ለአገር ክብር የቆመና ለኢትዮጵያ የሚቆረቆር መንግሥት አለን ወይ? የሚያስብል ነው፡፡ አሁንም መንግሥታችን የሻዕቢያ ጉዳይ ፈጻሚና ተላላኪ ነው ወይ? ከማስኘት አልፎ የቴሌቪዥን ሥርጭቱን ማቅረብም ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ቁስለት ነው እላለሁ፡፡
ነሐሴ 27 ቀን 2007 በወጣው ሪፖርተር ቁጥር 1601 ‹‹ታክሲ›› ዓምድ ላይ ‹‹እንዲህማ አይጨፈርብንም፤›› በሚል ርዕሰ ከቀረበው፣ ለዛና ቁም ነገር ካለው የታክሲ ውስጥ ጭውውት ተሳፋሪ አዛውንት እናት ለአንድ ወጣት የቴሌዥኑን ሥርጭት አስመልክቶ በቁጭት ያስልተላለፉትን የሚከተለውን መልዕክት ልቤ እየነደደ ነው ያነበብኩት፡፡
‹‹ይኼንን ቴሌቪዥን አላየህም? የሻዕቢያ ተላላኪዎች በስደተኝነት ስም ሲደነፉበት፡፡ የስንትና ስንት ወገኖቻችንን ደም የገበርንበትን የአገር አንድነት ተጋድሎ ሻዕቢያ በጓሮ በር ሲያራክስብን አላየህም? በወኪሎቹ አማካይነት የመገንጠል ጦርነቱን 54ኛ ዓመት በገዛ ቴሌቪዥናችን እየደነፉ ሲያከብሩበት አላየህም?›› ሲሉት ‹‹እንዲህማ አይጨፈርብንም›› ብሎ ወጣቱ በቁጭት ደነፋ፡፡
ይኼ አናዳጅ መልዕክት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቢተላለፍም ጥቂትም ቢሆኑ ለኢትዮጵያ አገራቸው ልዩ ፍቅር ያላቸው ኤርትራውያንን በአክብሮት ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ እንደ ብርቅ ከምጠቅሳቸው፣ ለኢትዮጵያ መስዋዕት ከሆኑ ውድ የኤርትራ ጀግኖች መካከል ለዘርዓይ ደረስ፣ ለአብረሃም ደቦጭና ለሞገስ አስገዶም ትልቅ አክብሮት አለኝ፡፡ ኢትዮያዊነት ዜግነታቸውን ይዘው ለቆዩ የኤርትራ ልጆች ልዩ ወንድማዊ ፍቅሬን እገልጻለሁ፡፡ የመንግሥት ኃላፊነት በአገር መቀለድ አይደለም፡፡ ለኢትዮጵያ የሚቆረቆር መንግሥት እንፈልጋለን፡፡ ተጠያቂነት ይኑር በአገር አይቀለድ፡፡
(ከኢትዮጵያ ልጅ)

ወይዘሮ ቆንጅት፥ጠላቶቻችን ገና አላወቅናቸውም።በቅኝ ግዛት ስር እንዳለን የተገነዘብነው በጣም ጥቂቶቻችን ነን።በዚህ አጋጣሚ ለኦሮሞ አገር ወዳዶች አንድ እጅግ ወቅታዊ የሆነ ጥሪ ላስተላልፍ።
ውድ አገርወዳድ የኦሮሞ ልጆች፥
ባለፉት ተከታታይ ስረአቶች በተፈፀሙት እጅግ የሚሰቀጥጡ ሰባአዊ እና ፖለቲካዊ የመብት ጥሰቶች እያንዳንዱ genuine ኢትዮጵያዊ የሚያፍርበትና አንገቱንም የሚደፋበት የታሪካችንም ጠባሳ የሆነበት ነው። የዚኣ ትውልድ የታሪክ ባለቤትና ተሸካሚ አሁን completely ሞቱኣል ማለት ባንችልም የመጨርሻ እስትንፋሱን እየወሰደ ነው ብየ መናገር እችላልሁ። Now ይኽነን ካልኩ ብሁዋላ ግን አንድ ጥሪ ለ genuine ኦሮሞ ልጆች አንድ ጥሪ ላስተላልፍ።
ወያኔ አጥንታችን ቆርጥሞ ደማችን መጦ እየጨረስን ያለው በኣማራ እና በኦሮሞ መካከል ጥላቻ በመዝራት ነው።ዛሬ የአማራ እሴት እንዳትወልድ የዘር ማጥፊያ መድሃኒት እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ወያኔ የዘር ማጥፋቱን ወንጀ በስፋት እየፈፀመ ያለበት ሁኔታ ነው።የኦሮሞ አፈር ትግራይን ለማልማት በጨልማ እየተጫነ መሆኑን ማንኛችንም የምንገነዘበው ነው።የአማራውን ለም መሬት ወደራሳቸው ጠቅለው ወስደውት አማራውን ጦም አዳሪ ካደረጉት ዓመታት ተቆጥርዋል። እኔ የኦሮሞ ሕዝብ መግንጠል ይበጀኛል ብሎ ክወሰነ I will totally endorse that.I also hope those non-oromo inhabitants in the oromo territory will receive a fair treatment to be able to live where ever they are just like any other oromo.በመጨረሻም እኛ ማለትም ኦሮሞና አማራ አንድ ላይ ከቆምን የወያኔ እድሜ በፍጥነት ወደሞት ይቃረባል ብየ አምናልሁ።ይኽነን ነገ ሳይሆን ዛሬውኑ ማድረግ ይጠበቅብናል።የሕዝባችን ሰቆቃ ለማሳጠር ከፈለግን።ስለጊዜያችሁ አመስግኘ ልጨርስ።
Haji Mansur al habeshi do not play with oromo.think your neftegna ortodox.you are the killer minelik
oromo and amara alliance (የትግል አጋርንት) is a must and this is a night mare for tplf criminals and this response can not be from any rational oromo man.
Eritrean are heroes and you know that and all they have had done for Ethiopia it is nothing for you “Hodama”:They have own land and the Sea so they have nothing with Ethiopia to do.Erfesh Tekemechi Dulie”
አንተ የጣሊያን ቅኝ ተገዥ ኤርትራዊ አርፈህ ዝም በል:አሁን ኤርትራ ሀገር ሁና ነው እንዲህ ምታካብድ!ኢትዮጵያ ማለት ነፃነት ማለት ነው:ኤርትራ ግን ባርነት ማለት ነው:ልጅ አባቱን በርግጫ የሚማታበት ዘመን ሁኖ እንጂ እንዲህ አጠብርም ነበር:ምድረ የፈረንጅ ሎሌ!!
Listen have you ever noticed the werkit (orommo)leader did what gragn mehamed did ,orommo’s were conquering The rest of Ethiopians from south to North were stopped at wollo (kallo Awraja).you have taken all the lands of the rest of Ethiopians .Don’t complain think of cause & effect orommos never got mistreated different from the rest of Ethiopians.so let us leave together by saying bygone Is bygone.
konjit, dibin alshi aydel tekatelsh esey.tifenijiyalesh enji minim atamechim wusha.
ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል በጊዜ አስነጥፎ
ሲያዘግም ያመሻል
ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል በጊዜ አስነጥፎ
ሲያዘግም ያመሻል
Bravo
YOU RIGHT YAGER LIJ ETHIOPIA LEAD BY ERITREAN
ሻቢያ የአረቡ ሰረገላ ነው:ባሪያ ነበሩ ወደ ባርነት ይመለሳሉ(ሻቢያወች)