ከስህተት ወደ ጥፋት የተሸጋገረው የቋንቋ ግድፈታችን! (የትነበርክ ታደለ)

ከቅርብ አመታት ወዲህ በሀገሪቱ ውስጥ እየታየ ያለው የቋንቋ ግድፈትና የቋንቋ አጠቃቀም ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ህጻናትን “አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር ሁለቱም ወንጀል ናቸው።” ብሎ እስከ ማስተማር የደረሱ ትምህርት ቤቶችን አፈራን። ስህተት ነው ይታረም ስንል ተንጫጫን~ ችግሩ ግን ዛሬም ድረስ ተሸፋፍኖ እንዳለ ነው።

ቀጠለና በየአደባባይ የምንለጥፋቸው የህዝብ ማስታወቂያዎች ላይም ስህተት የማይመስሉና ሆን ተብለው የሚደረጉ እስኪመስሉ ድረስ ቃላት ማጣመምና ፊደላት መግደፍን ስራዬ ብለን ተያያዝነው። ለዚህም የትኛውም የሚመለከተው ክፍል መልስ ሳይሰጥ እኛም በዋዛ ፈዛዛ አለፍነው።

በተለይ ደግሞ ሰሞኑን የኤሌክትሪክ ባቡሩን ስራ መጀመር ተከትሎ ለአካባቢ መለያነት የተለጠፉት ታፔላዎች ፍጹም ወንጀል በሆነ መልኩ በሁሉም አቅጣጫዎች በህዝብ ፊት ተለጣጥፈው እያየን ነው። ለዚህም እስካሁን ሀላፊነት የወሰደ አላየንም።

እነዚህን እንደ ተራ ስህተት ብንወስዳቸውም ከጅምሩም እንዳይፈጠሩ ብቃት ባላቸው ሰዎች ማሰራት ይቻል ነበር።

ከሁሉ በላይ የሚያሳስበው ግን ለዘመናት ራሱን ችሎ ለብዙ አዳዲስ ጽንሰ ሀሳቦችም ሆነ ቁስ አካል ሁነቶች ስያሜ ሲወልድ የኖረን ቋንቋ በፍጹም ሊወከል በማይገባው በባእዳን ቋንቋ ሲተካ ማየት ከግርምትም በላይ እጅግ በጣም ይከነክናል።

አሁን “የህዝብ መጓጓዣ” የሚለውን ሀረግ “ፐብሊክ ትራንስፖርት” ብሎ ማለት ምን ማለት ነው? ያውም በቋንቋው ፊደላት። ይህ ምንድነው? ስንፍና? ንቀት? ምን አገባኝ? ምን ታመጣላችሁ? ጥላቻ? ወይስ ምን?

እጅግ በጣም ይገርማል! ይህ ስርአት ራሱን ከሚገልጽበት ዋናው ባህሪ የቋንቋን መብት ማስከበር ነው። ሀገር ወለድ ቋንቋዎች በትምህርትና በጥናት ተደግፈው እንዲያድጉና ተናጋሪዎቹም ያለምንም መሸማቀቅ እንዲገለገሉበት ማስቻል “በትግል አስገኘሁት” የሚለው አንዱ ውጤት ነው።

አማርኛ ቋንቋ ደግሞ የፌደራል የስራ ቋንቋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ይበልጥ ጥበቃና ክብካቤ ሊደረግለት የሚገባና ሁላችንም ጥብቅና ልንቆምለት የሚገባ እንጂ እንዲህ መዘባበቻ ሊሆን የሚገባው ቋንቋ አይደለም። በፍጹም!!

እና ምንድነው የምንሰማውና የምናየው ነገር? ለምንድነው ለምንፈጥራቸው ችግሮች ሀላፊነት የማንወስደው? ለምንድነው ያለንን ነገር ለመጣልና ለማስጣል የምንራወጠው? ለምን?

ይህ የፖለቲካ ጥያቄ አይደለም! እንደ ቋንቋ መምህርነቴ ፊደል አስጠንቼ፣ ቃላት አስመስርቼ አረፍተ ነገር ብሎም አንቀጽ ጻፉ ብዬ ያስተማርኳቸው ተማሪዎች እንዲህ ያለ የሁለተኛ ክፍል ተማሪ የማይሰራውን አይነት ስህተት በየጎዳናውና በየአገልግሎት መስጫው ሲገጥማቸው ሳይ እኔ ስለነሱ አዝናለሁ።

ይህ ደግሞ ቀስ በቀስ ሊያመጣ የሚችለውን ሀገራዊ የቋንቋ ግድ የለሽነት መዘንጋት ነው!። ይህ እያወቅን የሰደድነው እሳት ነውና በጊዜ ልናጠፋው ይገባል! በጊዜ! አሁን ነገሩ ከስህተት ወደ ጥፋት አድጓልና! [From Error to Mistake then a crime!]

Yetneberk Tadele's photo.

13 Comments on “ከስህተት ወደ ጥፋት የተሸጋገረው የቋንቋ ግድፈታችን! (የትነበርክ ታደለ)”

  1. ወንድሜ ለገሰ ዜናዊ ለሄርማን ኮል የተናገረው ምንድነው
    የሶሻሊዝምን ፅንሰ ሀሳብ ከሀገራችን ለማጥፋት 50 አመት ላይፈጅብን ይችላል
    አማራንና አማርኛን ከኦርቶዶክስ ዕምነት ጭምር ለማጥፋት ቢያንስ መቶ አመት ያስፈልገናል ብሎ መክሯል ይባላል።
    ሆን ተብሎ ነው ግድፈቱ የሚደረገው።

  2. I think it is sufficient to know the depth our failure in Amharic language by simply looking at the new name and logo of Ethiopian radio and television. You can find nothing in Amharic including the letters.

  3. Nom more ethiopia is ortodox and amara state.you neftegna accepte oromo tigre welayta gambela and more i hope one day no amharic in my land oromya.if you want amharic and ortodox go to your blessed land Gonder

  4. There is a saying, think globally live locally,but I say “Think globally and speak globally live globally” don’t be narrow minded..language is a tool to comunicate with so instead of comunicating with 26 million amaras by lerning amharic why don’t we comunicate with a billion english speakers!!!!!to get more economic and political benefits!!!!

  5. እናንተ ደደብ ወያኔዎች ሆን ብላችሁ የሀገራችንን ቋንቋ ባህል ትውፊት

    የምታዳክሙ ሁላ ከዚህ ተግባራችሁ ተቆጠቡ የህዝብ ንብረት የሆነውንም

    አውቶቡሥ ሠማያዊውን ማለቴ ነው እንዲሁ ፕብሊክ በማለት የባንዳ

    ሽርደዳቸውን ያቁሙ ምላሹ የከፉ ነውና የባንዲራው ይበቃናል

    እሥከግዜው።

    ፈረንጆቹ ይህን ይላሉ THINK BEFORE YOU INK!!!

  6. የባንዳ ካድሬ ይህን ካልተናገረ ወያኔ አይባልም

    ኤጀንሢ

    ዲያሥፖራ

    ኢንቬሥተር

    ኢንቨሥትመንት

    ኮንዶሚንየም

    ኤክሥፖርት

    ተርሚናል

    እሥቴሽን…..ወዘተ በ24 አመታት ብረዛውን በየሚድያው ሢያንቧርቅ ታይቷል ምንም የመሻሻል አዝማሚያ ፈፅሞ አይታይም።

  7. የአምሥት አመት የኤክሥቴንሽን መርሀግብር

    የአምሥት አመት የትራንሥፎርሜሽን

    በጣም በርካታ የመንግሥት ተቋማት የቋንቋ ግድፈት የተመፃወታቸው ናቸው ይህ ከሥርአቱ የውንብድና አሥተዳደር የመነጨ ነው።

  8. gimgondere you’re fucken stupid.Don’t ever use this kinds of name to insult Gonder people.There are no gimgonder people in the provience of Gondar but there are patriotic & clean Gondare.

  9. @gimgondere

    አይተ ወያኔ ወዲ ሸርሙጣ

    በሀይማኖት በብሄር ለመበታተን ካሠባችሁ መቀበሪያችሁን ፈልጉ የሙት

    ነፍሥ ምሪት ቅዥት ነው እኔ በግሌ የመለስን ሬሣ እንደቢላደን

    እንደማቃጥለው ልንገራችሁ እንናንት የኢትዬጵያ ባንዳ ወያኔዎች ዋ

    ከድርጊታችሁ ታቀቡ።

  10. ስንት የአማራ እክስትርምስት አለ የአማራው ህዝብ ከነ ህይወቱ የት እንደ ገባና የት እንደደረሰ የማይታወቅ እያለ ስለ ፊደል መወላገድ ይበልጥመጨናነቅና ሃታካሮ መብዛት ምን ፈይዳ አለው.ካልሆነ በ እንግልዘኛና በ አፋን ኦሮሞ ይደረግና. እክስትርምስት አማራዎችን ዝም መድረግ አልያም ካልሆነ በትግርኛ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*