የአቶ ዳዊት ገ/ሔር ቤት በአሸዋ ላይ ወይስ በዓለት? (ስሉሥ ወልደሂወት)

ከሰሞኑ አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር የተባሉ ዜጋ በተለየ ሁኔታ በህወሓትና ህወሓት በሚመራው የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የልማትና መልካም አስተዳደር ፖሊዎችና አፈጻጸም ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ፡፡ የአቶ ዳዊት ትችት ከግል ገጠመኝና ትዝብት በመነሳት በአጠቃላይ በስርዓቱ፣ ስርዓቱ በቆመባቸው ምሰሶችና የማስፈፀምያ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎች እንደዚሁም የድርጅቱና የድርጅቱ አመራር ዓቅምና ህዝባዊነት ላይ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልኩት ከፖሊሲ የተሻለ ፖሊሲ፣ ከተሻለው ፖሊሲ እጅግ የተሻለ ፖሊሲ መኖሩ የማይቀር ስለሆነ፤ አቶ ዳዊት ስለተሻለ አመራር፣ […]