የተፈቱ እስረኞች በማያቋርጥ የትግል ውጤት ሂደት እንጂ በወያኔ የዋህነት አይደለም::

Minilik Salsawi – መጀመሪያ ማወቅ ያለብን የማያቋርጠው ትግላችን ፍሬ እያፈራ መሆኑን እና ጥንካሬን እያላበሰን መሆኑን አንዘንጋ::በአዲስ አመት 2008 መምጫ ላይ የወያኔው ጉጅሌ መንግስት በሰጠው መግለጫ (በምሕረት?)ፈታሄቸው ያላቸው ኢትዮጵያውያን እስረኞች የተፈተቱት ሕዝቦች ግፍን ላለመቀበል በጋራ ባደረጉት ትግል ጫና እንጂ በወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ የዋህነት አሊያም ሆደ ሰፊነት አይደለም::ከዚህ ቀደምም የጦማርያን እና ጋዜጠኞች መፈታት የሕዝብ እና የምእራባውያን ጫና እንደነበረበት የማይዘነጋ እውነት ሲሆን ከቀድሞ ጊዜ ጀምሮ ወያኔ አጣብቂኝ እና ጫናው ሲበዛበት ይህንን እንደሚያደርግ የታወቀ ጉዳይ ነው::

ወያኔ ሆደ ሰፊ ነው ማለት ሞኝነት ነው::ወያኔ መሰሪ እና እባብ ነው:;እንኳን የሚሰራውን ግፍ የሚቃወሙትን ይቅር እና አይናቸው ያላማረውን የራዙን ሰዎች የሚበላ ማፊያ ድርጅት ነው:: በምህረት የተፈቱ እስረኞች ሁሉ የማያቋርጠው የትግላችን ውጤት እንጂ በወያኔ መልካምነት አሊያም የዋህነት ምህረት እና ይቅርታ አይደለም::አሁንም ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል በየእስር ቤቱ የታሰሩ ወገኖቻችን ሁሉ እንዲፈቱ ጫና በመፍጠር እንዲሁም በኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ በመተባበር የዜግነት ግዴታችንን እንቀጥል::የጋራ ጠላታችን ወያኔን በመደምሰስ ለተሻለች ህዝባዊት ኢትዮጵያ እንረባረብ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬