የትግላችን መነሻ ምንድን ነው ? በአሁኑ ሰአት በየ አካባቢያችን ምን እየተከናወነ ነው ? (አብዱረሂም አህመድ:BBN)

አባቶቻችንን የተማርንባቸውን መድረሳዎች ለመስራት እና እዚህ ለማድረስ ከፍተኛ መስዋእትነት እንደ ከፈሉ ታሪካቸውን ሲነግሩን እና ያለፉትን ስርአቶች ጋር ተናንቀው እዚህ እንዳደረሱት የማይካድ ሃቅ ነው ፡፡ በሀገራችን መስጅዶችና መድረሳዎች ባለፉት ስርአት ደም ፈሶባቸዋል አጥንት ተክስክሶባቸዋል፡፡
መስጅዶችና ኢስላማዊ ትምህርት ቤቶችን እዚህ ለማድረስ በርካታ አባቶች ብዙ መስዋእትነት ከፍለዋል፡፡ ከሃይለ ስላሴም ከደርግም ጋር ተናንቀው እዚህ መድረሳቸውን ታሪካቸውን ሲነግሩን እድለኛ ሁኞ የተማርኩበትን መድረሳ የትምህርት ቤቱን ዶክመንተሪ ሲሰራ ለማወቅ ችያለሁ፡፡ ሁሉም መድረሳና መስጅዶች ታሪካቸው ተመሳሳይ ነው ዋጋ ተክፍሎባቸዋል::


የሚያሳዝነው ነገር አሁን የደረሰንበት ስርአት ደግሞ አባቶቻችን ዋጋ ከፍለው የሰሩት መድረሳዎች ላይ የአህባሽን አስተምህሮ ካላጠመኩበት እያለ ትግል ላይ ነን፡፡ እውነት ግን እኔን ጨምሮ የምጠይቀው አንድ ጥያቄ አባቶቻችን እዚህ ያደረሱን መድረሳዎች ለመጠበቅ ምን ያህል ዝግጁ ነን ?የዲሞክራሲ ሰባኪው ኢህአዴግ አካሄዱ እጅግ አደገኛና ትውልድን የመበረዝና የመመረዝ ሴራ ነው፡፡ ይህንን ደግሞ በትምህርት ቤቶች ዙርያ ያሉም ሆነ ወላጆች ጠንቅቀው መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ አንዳንዴ በእለት የምንገኛትን ብቻ እያሰብን መጪውን ትውልድ ለማጥፋት እየሰራ ያለውን አህባሽን እንዘነገዋለን፡፡ እናም ሁላችንም በየአካባቢያችን ምን እየተካሄደ ነው ታናናሾቻችን፤ወንድምና እህቶች የሚማሩበት መድረሳ ምን እያስተማሯቸው ይህን መጠየቅ አለብን፡፡


አንዳንድ መድረሳዎች ላይ የአህባሽ አስተምሮን ቁርአን እያሉ እንደሚያስተምሯችው የተመረዙ ነሽዳዎችን እንደሚያስጠንዋቸው በድምጽም በቪዲዪ ካየናቸው መረጃዎች መረዳት ተችሏል፡፡ እናም እነዚህን ልብ ብሎ መከታተል በተለይም የአሊሞች፤የወላጆች ሃላፊነት ነው
በነገራችን ላይ የጀመረነው ትግል የታሰሩትን ማስፈታት አይደለም፡፡ የታሰሩትን ማስፈታት አራተኛ ጥያቄያችን ነው ትልቁ ዋናው ትግላችን ትውልድን ማዳን ኢስላምን መጠበቅ መሆኑን ፈጽሞ መዘንጋት የለብንም ወላሁ አእለም
አብዱረሂም አህመድ