የዓመቱ ዐቢይ ስኬት – በሕግ ተጠያቂ ስለሚኾኑ አማሳኞች ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ለአጥኚ ኮሚቴው አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ!
- ማስረጃዎች ለሕጋዊ ጥያቄ በሚያመቹበት ኹኔታ በአፋጣኝ ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ታዟል
- በጥምር እና በተናጠል ተጠያቂ የሚኾኑ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች በስም ዝርዝር ይለያሉ
- የቤት እና የመኪና ሽልማት የተሰጣቸው አለቆች እና የስጦታው ምክንያት ተብራርቶ ይቀርባል
* * *
- የመሬት፣ የሕንጻ እና የልማት ይዞታዎች የኪራይ ውላቸው ለአንድ ዓመት ብቻ ይኾናል
- ከሦስተኛ ወገኖች ጋር ለመዋዋል እንዲቻል የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በቋሚ ሲኖዶሱ ጸድቋል
- የቤትና የመኪና ሽልማት ለፓትርያርኩ ቀርቦ በቋሚ ሲኖዶስ ሳይጸድቅ እንዳይፈጸም ተወስኗል
* * *
- ጥናቱ ከመቶ በላይ የገዳማትና የአድባራት የመሬትና የሕንጻ አጠቃቀም ችግሮች ላይ ይቀጥላል
- አማሳኞች÷ ከስም ማጥፋት፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ያለፈ አካላዊ ጥቃት ለመፈጸም እያቀዱ ነው
