የሕወሓትን ጓዳ ከነጫጩቶቿ ያንቀጠቀጠው የፕሮፌሰር መስፍን አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የሕወሓትን ጓዳ ከነጫጩቶቿ ያንቀጠቀጠው የፕሮፌሰር መስፍን አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ  (ምንሊክ ሳልሳዊ)
አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ

ሰሞናኛ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ አሸብረው የተሸበሩ የዘረኛ ቡድን ካድሬ የሆኑ የሕወሓት ጫጩቶች የማህበራዊ ሚዲያ ጫጫታ ነው::ምሁር በሽታቸው የሆነ ሕወሓቶች ጫጫታቸው ያተኮረው በፕሮፌሰር መስፍን ላይ መሆኑ ምን ያህል በበታችነት ዛሬም እንደሚያላዝኑ ያሳየ ነው::ፕሮፌሰር መስፍን አዳፍኔ የተባለውን የእኩይ ፖለቲከኞችን ሴራ ፍንትው አድርገው ያሳዩበት መጽሃፍ ከወጣ ጀምሮ ተራሮችን አንቀጠቀጥኩ የሚሉት እነአግበስብሴ ከነጫጩቶቻቸው ዘራፋቸውን ከመጀመራቸውም ሌላ መጽሃፉን የመተቸት/የመገምገም አቅሙ ስላሌላቸው የግለሰብን ሰብእና እስከመንካት ዘልቀዋል::ይህ የሚያሳየው የፕሮፌሰሩ አዳፍኔ የሕወሓትን ጓዳ ምን ያህል እንዳንቀጠቀጠ ነው::

ኢትዮጵያዊው ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ሲጽፉን ሲናገሩም የመጀመሪያቸው አይደለም::ሌሎችን ኢትዮጵያውያን ምሁራን እና ፖለቲከኞች በዘረኞች እና በእኩይ ፖለቲከኞች ላይ መጽሃፍትን ጽፈዋል::የአዳፍኔ ግን በተለየ ሁኔታ የሕወሓትን ቤት አናግቶታል::ሕወሓቶች ከጫፍ እስከ ጫፍ ፕሮፌሰሩ ላይ አፋቸውን አሹለው መነሳታቸው ያለቸው የፖለቲካ እምነት በበታችነት እና በዘረኝነት ላይ ስለተመሰረተ ተዳፍኖ ሳይቀር ስለተጋለጠባቸው መቆምያ መቀመጫ ሲያጡ ታዝበናቸዋል::የሕወሓት ፖለቲካ ምን ያህል በጥቂቶች የዘረኛ አስተሳስብ ላይ እንደተመሰረተ እያየን ያለንበት ሁኔታ ላይ ነው ያለነው::ሕወሕቶች ከነጫጩቶቻቸው ምነው እንዲህ ተራወጡ? የሚጽፉት ሰዎች ደሞ አንድ ወጥ የሆኑ ለምን ሆኑ? ብአዴኖች ኦሕዴዶች የት ገቡ ? ማን የበታችነት ስሜት ውስጥ ዘረኝነትን እንደሚዘፍቅ አዳፍኔ በተግባር እያሳየን ነው:: እድሜ እና ጤና ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም::ኣቦ ተባረክ !!! Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

Minilik Salsawi's photo.