አማራው የህወሓት ቼ ጉቬራ (ከህወሓት አስራ አንዱ መስራቾች አንዱ ጎንደሬ ነው)
ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
አማራው የህወሓት ቼ ጉቬራ
ፋኖ ተሠማራ… ፋኖ ተሠማራ…
እንደ ሆቺሚኒ… እንደ ቼ ጉቬራ…
በዱር በገደሉ ታሪክ ልትሰራ
ዛሬ ፋኖ ወደ ዱርም፣ ወደ ገደልም አይሰማራም፡፡ አለመሰማራት ብቻ አይደለም፡-
‹‹ፋኖ፣ ፋኖ፣… ኧረ ፋኖ… ጥራኝ ጫካው፣ ጥራኝ ዱሩ
ለአንተም ይሻልሀል ብቻ ከማደሩ
ፋኖ፣ ፋኖ፣ ኧረ ፋኖ፣ ፋኖ… የሚል ዘፈንም አይዘፍንም፡፡ የቱንም ያህል መብትህ ቢገፈፍም፣ ድምፅ ቢጭበረበርም አንተም አታንጎራጉረው፡፡ ሌላው ቀርቶ እነዚህ መብቶች ቅንጦት ናቸው ብለን ብናልፋቸው እንኳ ቢርበህ እና ቢጠማህም ‹‹ፋኖ፣ ፋኖ፣ አረ ፋኖ…›› ብለህ አትዘፍንም፡፡