የዳግማዊ አፄ ምኒልክን እና የእቴጌ ጣይቱ ብጡልን ታሪክ አዛብቶ ማቅረብ ለምን አስፈለገ?

ተድላ ሀይሉ

ሰላም ውድ አንባብያን። ሠሞኑን አንድ ጽሑፍ በአቶ ተስፋዬ ገብረአብ ተደርሶ በኢንተርኔት በየድረ-ገፆቹ ተበትኗል። የዚህ ጽሑፍ ትክክለኝነት ወይም ተዓማኒነት ሣይጣራ ልክ እንደ ቆላ ሠደድ እሣት በብዙ የኢትዮጵያውያን ድረ -ገፆች ላይ ተበትኗል። ነገር ግን ‘ታሪክም’ ይሁን ‘ድርሠት’ ሆን ተብሎ የሚታወቅ ሃቅን ለማስካድ የሚጻፍ ከሆነ አንባብያንን ማሣሣት ብቻ ሣይሆን በትውልድ ውስጥ የማያስፈልግ ውዝግብን ይተክላል።