አቶ በረከት ስምኦን በማሌዢያ ፒናንግ ደሴት የንግድ እና መኖሪያ ሕንጻ ቤት እያስገነቡ ነው::
አቶ በረከት ስምኦን በማሌዢያ ፒናንግ ደሴት የንግድ እና መኖሪያ ሕንጻ ቤት እያስገነቡ ነው:: –
Minilik Salsawi – የለውጥ ሃይሉ እርስ በእርሱ በፖለቲካ ጥላቻ ሲጠዛጠዝ በሃገር እና ሕዝብ ላይ ዘረፋው ቀጥሏል:-ከጸረ – ሙስና ኮሚሽን ከመዝገብ ቁጥር /203/2007 ከተገኘው መረጃ መሰረት አቶ በረከት ስምኦን በማሌዥያ ፒናንግ ደሴት ጃላን ባሩው 62 በተባለ ቦታ ላይ በሚሊዮኖች ዶላር በወጣ ወጪ ኢትዮጵያ ውስጥ በብረታብረት ስራዎች ላይ ከሚገንኝ አንድ ማሌዢያዊ ጋር በመቀናጀት እጅግ ዘመናዊ የንግድ እና መኖሪያ ሕንጻ በኢንቨስትመት ስም እያስገነቡ መሆኑን ጥቆማ ለኮሚሽኑ ደርሶ በመመዝገብ እያጣራ መሆኑ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::ከሼህ መሃመድ አላሙዲ የሃገሪቱን ሃብት እያሳለፉ እየሰጡ ከፍተኛ ገንዘብ የሚረከቡት ኤርትራዊው አቶ በረከት ስምኦን በግልጽ ከሚታወቀው ከአገር ቤቱ በካፒቴኑ ስም ካስመዘገቡት ሆቴል እና ማደያዎች እንዲሁም የሪያል ስቴቶች በተጨማሪ በዱባይ እና አቡዳቢ መኖሪያቤቶች እና አክሲዮኖች ሲኖሯቸው እንዲሁም በሚላን ጣሊያን መኖሪያ ቤት በሕንድ የሚስማር ፋብሪካ ባለድርሻ ናቸው የሚል ከዚህ ቀደም በጸረ ሙስና ኮሚሽን የተመዘገበ ፋይል አላቸው::
የጸረ ሙስና ኮሚሽን በሕወሓት ባለስልጣናት በተለይ በአቶ ደብረጽዮን እና በጄኔራል? ሳሞራ ልዩ ትእዛዝ የሚመራ ሲሆን በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የሚመጡ መዝገቦች ከቦታቸው እንዳይንቅሳቀሱ እና ተጣርተው ማረጋገጫ እንደተገኘ ከነማስረጃቸው ታሽገው ቀጥታ ወደ ደህንነት ቢሮ እደሚላኩ ይታወቃል::የአቶ በረከት የመኖሪያ ቤት ግንባታም ጠቅላላ መዝገቡ እንዳለቀ በጥብቅ ምስጢር በሚል ለደህንነት ቢሮ እንደሚላክ ምጮቹ የጠቆሙ ሲሆን የከፍተኛ ባለስልጣናትን ጉዳይ በሚመረምሩ መርማሪያን ላይ ክፍተኛ የሆነ የደህንነት ክትትል እንደሚደረግ ምንጮቹ አክለው ጠቁምዋል::
የደህንነት ቢሮው በቅርቡ ያወጣቸው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ባለስልጣኖች በተለያዩ ሃገራት የሰሯቸው መኖሪያ ሕንጻዎች መታገዳቸው ይታወቃል::የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኬንያ እና ሱዳንን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት መኖሪያ ቤቶች የሰሩ ሲሆን በታንጋኒካ ውስጥ ሃይቅ ዳርቻ ላይ የግል የመዝናኛ ቦታ ለመገንባት ያመለከቱ የሕወሓት ባለስልጣናት ከታንጋኒካ ባለስልጣናት ጋር በቦታ መረጣ እና በጉቦ ገንዘብ አለመግባባት እስካሁን እንዳልተፈቀደላቸው ታውቋል:: #ምንሊክሳልሳዊ

ይህ ነው የምርጥ INVESTIGATIVE JOURNALIST ብቃት በርታ !!!
መቼም ምን ብለው እንደሚያሥተባብሉ ለመሥማት ቸኩያለሁ ይህ ነው ወያኔ ተፈረካክሷል የምንለው 15 ቀን በላይ የፈጆ ሥልታዊ ማፈግፈግ ሥብሠባ ለሀገር ተጨንቀው ሣይሆን በደምና በመክሊት ሚዛን ደፍተው የኢትዬጵያን ፍርድ በመጠባበቅ ላይ ናቸው በግሌ ማንኛውንም ጋዜጠኛ የማሣሥበው መረጃውን በአግባቡ ይዞልን እንዲያቆይ የዜግነቱን ግዴታ እሥከ ሠአቱ በታማኝነት እንዲይዝ እጠይቃለሁ።
ድል ለኢትዬጵያ !!!
እግዚያብሄር ኢትዬጵያን ይባርክ!!!
If this news comes from minilik salsawi it’s beriewolede.
bertu yqetlal gena bizu taric ale
bertu gena bizu taric ale
why do we need to accuse people without relevant evidence …..it’s only weaken our struggle for freedom and democracy we don’t need to follow individuals. Berekt is a clinical dead person.
kemenlik salsawi min ytebekal beka wishet bicha.demo atafrim ertrawi tlaleh.ante gin ye america zegnet aleh.wishetam.and neger yekereh neger kale ethiopia wist semay ferese,ethiopia 90 millions sew mote,wishetam.
He is our hero
ሠብ #ምንሊክሳልሳዊ የእውነት መቅረዝ !!!
RIP weyane
best
ሠብ #ምንሊክ ሳልሳዊ ናይ ህቂ ላምባ !!!
ሀቅ እዩ ወዲ ሣልሣዊ አጆሀ !!!
ወያናይ ተዋሪዱ ደቂሦም አብ ገዛ
ፅቡቅ ወዲ እዩ አይ ትዝሀራረቡ ብዙህ
አጆሀ ምንሊክ !!!……..