የኢትዮጵያ የስደት መንግስት፤ ከህሳቤ ወደ ተግባራዊነት

entc and eynm logo
የኢትዮጵያ የስደት መንግስት መመስረት አስፈላጊነት ላለፉት ሁለት አስርት አመታት፣ በተለይ ደግሞ የግንቦት 1997 ዓ.ም. ሃገራዊ ምርጫን የህወሃት/ኢህአዴግ ስርዓት በጠመንጃ አፈሙዝ ከህዝብ መንጠቁን ተከትሎ ውይይትና ክርክር ሲደረግበት ቆይቷል። የተሰረቀውን የህዝብ ድምፅ ለማስመለስ የተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የተለያየ የትግል ስልት መከተልን መርጠዋል። አንዳንዶች የትጥቅ ትግል ሲመርጡ፣ ሌሎች የምርጫ ፖለቲካን ገፍተውበታል። የአፖርታይዱ ወያኔን አምባገነን ስርዓት አስወግዶ ሁሉም አቀፍ ህዝባዊ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም እስካሁን ያልተሞከረ መንገድ ቢኖር የፓርቲ ፖለቲካን ወደ ጎን በመተው ባለድርሻ አካላትን ሁሉ ያሳተፈ የስደት መንግስት መመስረቱ ነው።

ይህን ሃሳብ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሐምሌ 2012 እ.አ.አ. አያሌ ኢትዮጵያውያን በዳላስ ቴክሳስ በመሰባሰብ የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት መስርተዋል። የሽግግር ምክር ቤቱም ላለፉት 3 ዓመታት ሃሳቡን ለማስረፅና ስምምነት ለመድረስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በርካታ ስብሰባዎችና የምክክር ጉባዔዎች አካሂዷል።

ባሳለፍነው ወር ሐምሌ 2015 የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤቱና የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ ከተለያዩ የድርጅቶች ተወካዮችና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ለሁለት ቀናት በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት ካደረጉ በኋላ የኢትዮጵያ የስደት መንግስት አደራጅ ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማምተዋል።

በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ የስደት መንግስት አደራጅ ኮሚቴ በመመስረት ላይ ይገኛል። የመጀመሪያ መዋቅሩ ተዘጋጅቷል። የኮሚቴው ተቀዳሚ ስራ የሚሆነው፤ 1) የኢትዮጵያ የስደት መንግስት መመስረት አስፈላጊነትን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ 2) አስፈላጊ የሆኑ ህዝባዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና የፋይናንስ ድጋፎችን ማሰባሰብ፣ 3) የስደት መንግስቱን መሰረት መገንባት።

የስደት መንግስት ምስረታው ብዙ ደረጃዎች ይኖሩታል። የኢትዮጵያን ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት በጣም በጥንቃቄ ታቅዶ ጠንካራ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ኮሚቴው ይረዳል። በተጨማሪም ዘርፈ-ብዙ ስራዎችም እንዳሉት ይገነዘባል። በሚቀጥሉት ቀናትና ሣምንታት አደራጅ ኮሚቴው የነደፋቸውን እቅዶች ለህዝብ ይፋ በማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናል።

የኢትዮጵያ የስደት መንግስት የመጨረሻ ግብ የሚሆነው ኢትዮጵያ ውስጥ የተረጋጋ፣ ሰላማዊና ወደትክክለኛ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር መኖሩን ማረጋገጥ ነው። ከዚህ በፊት ያልታቀደ የስርዓት ለውጥ የሚያስከትለውን ቀውስ አይተናል። ለዚህ ደግሞ ሃገራችንን መመልከት በቂ ነው። በአሁን ወቅት በሶሪያና ሊቢያ እየሆነ ያለውን መመልከትም እንችላለን። ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጠነም ዘገየም ለውጥ መምጣቱ የማይቀር ነው — ምክንያቱም አምባገነን ስርዓትን ለመታገል ህዝብ በየትኛውም ሀገር ቢሆን ማመጹ ስለማይቀር። በተቻለ መጠን ሌላ ቀይ ሽብር፣ ሌላ አፖርታይድ ስርዓት፣ ሌላ የህዝብ እልቂት በሀገራችን እንዳይከሰት የሚመጣው ለውጥ በሰላማዊ ሂደት እንዲያልቅ እንፈልጋለን።

የታቀደ፣ የተደራጀና ሠላማዊ ለውጥ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲመሰረት በሚደረገው ጥረት ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንድትሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤትና የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ
ቀን 20/09/2015

ለግንኙነት፤
[email protected] or [email protected]

9 Comments on “የኢትዮጵያ የስደት መንግስት፤ ከህሳቤ ወደ ተግባራዊነት”

  1. A good idea if such an institution has its office in a country like South Africa.

    Why South Africa ?

    Well, Ethiopia and South Africa share a lot in common; common interests, common views and common aspirations.

    So, if the members of such an institution got influenced by the South African society or were even recruited as agents of South Africa the harm they could cause would be limited.

    Not so if such institution is based in ferenji lands, even worse in the USA, a great enemy of blacks and Ethiopia, because influences from those ferenji lands or effects of agents working for USA would be far harmful to Ethiopia.

    We all have made our observations. For example USA based Ethiopians lobbied to recognize debt borrowed by TPLF in post-TPLF Ethiopia. Most likely those Ethiopians were told by USA to say so, and by doing that they betrayed Ethiopia. Ethiopian interest would have been to declare such debt odious debt.

    That is just one example.

  2. Some of our top priorities in this period should be to make sure that such institutions are not infiltrated by,

    1. USA

    2. Eritrea

  3. ሀሣባችሁ ጥሩ ነው ግን በርካታ ድርጅቶች በወያኔ ሤራ ሢበተኑ አይተናል በምን ማጣሪያ ተጠቅማችሁ ሣይንሣዊ በሆነ መንገድ ተጠናክሮ ለማሥወገድ እንደምንችል ንድፈ ማሥተሩ ልክ እንደ አውቶሚክ ቁልፍ ውሥን መሆን ያለበትሢሆን ቀሪውን ተሣትፎ በሀሣብ በገንዘብ በመረጃ ሁሉም የዜግነቱን እንደሚወጣ አልጠራጠርም።

    ድል ለኢትዬጵያ ልጆች !!!

  4. ግን ወያኔ ለምን ዲሞክራሢ ከወጣባት ሀገር ግሪክ አይማርም ብቃት ላለው አካል ሥልጣን ሢሸጋገር ድንቅ ክሥተት የታየበት ነው እኔ ብቻ ሥትሉ የማትወጡት ማጥ ውሥጥ መሆናችሁን ተደጋግሞ እየተነገራችሁ ነው ግሪክን ኢኮኖሚ ኢትዬጵያን ደግሞ የጠባብነት የፍትህ የሙሥና ካንሠር ወያኔ መያዙን ተመርምሮ ያወቀው አልመሠለኝም።

  5. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው:

  6. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    ፆሙ ተገድፏል ስለዚህ ወጣቶች በላይ በላይ እንዳትበሉ:የስጋ ውፍረት የመንፈስ ክሳት ያመጣል!!!

  7. @ @

    ማን ሆነና የሉካንዳውን የቤት ምርጫና ቅርጫ የሚሻማው ወያኔ ወይሥ?…
    ገባ ብለን አይተነዋል አመለካከታችሁ በሙሥና በዘረኝነት ሥብ ተደፈነ ዛሬ ወገን ተርቦ እናንተ ሽንጥ የምታወርዱ ናችሁ።

    የሠማይና የምድሩ አምላክ ይፍረድባችሁ ።

  8. ከዘንድሮ ወጣት ሽማግሌ ይሻል:በጊዜ አስነጥፎ ሲያዘግም ያመሻል says:

    አንተም አራዳ እኔም አራዳ…ነብሴ ሞኝሽን ፈልጊ:ዳቦ አቅርቦ ላጥምድ ማለት ሞኝነት ነው:

  9. Former vice secretary of treasury Paul C. Roberts about USA :

    ” Paul Craig Roberts: “America Is A Gulag”

    Submitted on 08/21/2015

    America is a gulag. We are ruled by a government that is devoid of all morality, all integrity, all compassion, all justice. The government of the United States stands for one thing and one thing only: Evil.You are part of the new Captive Nation. “

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*