ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን በኬንያ ፖሊስ ተያዙ

በኬንያ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋሉት 100 ኢትዮጵያዊያን ትናንት አመሻሽ ላይ ነው፡፡በወጣትነት የእድሜ ክልል የሚገኙት ታሳሪዎቹ በተፋፈነ ሁኔታ በአንድ ትልቅ መኪና ተሳፍረው ወደ ናይሮቢ በመገስገስ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች በተደረገ ፍተሻ መያዛቸው ታውቋል፡፡ታሳሪዎቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት አቅደው የነበሩ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡ እንደ ዴይሊ ኔሽን ዘገባ ከሆነም ስደተኞቹ በሞያሌ በኩል በድብቅ በማለፍ ወደ መሩ ካውንቲ ማምራታቸውን መረጃ የነበራቸው የኬንያ ፖሊሶች በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው […]