ቃለ አዋዲና ፍልሰታን አስመልክተው ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በነጻነት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ የሰጡት ቃለ-መጠይቅ
በአቡነ ቴውፍሎስ ተረቅቆ በግ. ቀ. ኃይለ ሥላሴ ዘመን ጊዜ ታውጆ በደርግ ዘመን ሥራ ላይ የዋለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ (ቃለ አዋዲ) ዛሬ የሚታየውን የሰበካ ጉባኤ የተጀመረበት ነበር። ይህንን ታላቅ ተግባር ጫንቃቸው ላይ አርፎ ከነበሩት አባቶች መካካለ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከዚህ ዓለም የተለዩን አባ አበራ በቀለና አብረዋቸው እንዲሰሩ ከጠቅላይ ቤትክህነት የተመደቡት ሁለት ሊቃውንት ይገኙበታል። ከነዚህም አንዱ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ነበሩ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባዔ ተዘዋዋሪ አደራጅ አስተማሪ የነበሩት ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ስለ ቃለ አዋዲና የፍልሰታ መንፈሳዊና ታሪካዊ ትስስር እግረ መንገዳቸውን በዚህ ቃለ መጥይቅ ይዳስሳሉ። ሙሉውን ቃለ መጠይቅ የሚቀጥለውን ሰንሰለት በመጫን ያዳምጡ።
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ከነጻነት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ከነጻነት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ
