ምሩቃን እና የሥራ ዕድል

በኢትዮጵያ ከሚገኙት ከ30 ከሚበልጡት የመንግሥት እና በብዛት ከተከፈቱት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዘንድሮ ከ90 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎች ተመርቀዋል። ዩኒቨርሲቲዎቸች እና የኮሌጆች ምሩቃን የቀሰሙትን እውቀት እና በሥልጠና ያገኙትን ሙያዊ ክሂሎት የተሻለ ኑሮ እድል ከፋች አድርገው ተመልክተውታል። ይሁንና፣ ገሀዱ እንደጠበቁት ሆና ሳያገኙት ቀርተው ብዙዎች ለስራ አጥነት መዳረጋቸውን ይናገራሉ። ምሩቃኑ ሥራ የማግኘት እድላቸው እስከምን ድረስ ነው? ችግራቸውን ለማቃለል ምን ሊደረግ ይቻላል? ውይይት አካሂደናል። Listen