ጋዜጠኛ ደምስ እና ተያያዥ ጉዳዮች
ይህ ጽሁፍ ቀደም ሲል ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ሄኖክ ሰማ እግዚሀር (የቪኦኤ ጋዜጠኛ) መብቱ ነዉ በሚለዉ መጣጥፉና በኤርትራ በኩል ኢትዮጵያን ነጻ ማዉጣት ሊታሰብ የማይቻል ነዉ ተብሎ የሚቀረበዉ ሀሳብ በማይመቻቸዉ ወገኖች ላይ ከሞላ ጎደል የተነጣጠረ ድርሳን ነዉ።
ጋዜጠኛ ደምስ አከታትሎ በኤርትራ በኩል የሚደረገዉ የነጻነት ጉዞ አልጣመኝም በማለት ቀደም ሲል ከጻፈዉ ጽሁፍ በተጨማሪ ሁለተኛዉ መጣጥፉን ይዞ ብቅ አለ ሶስተኛዉንም ደገመ ቃለ መጠይቅም ለቀቀ። ይህ ደግሞ ሊቃረኑት የሚከበድ ትንታኔና የፎቶግራፍ ማስረጃ በማስደገፉ ለተቺዎቹ የሚመች ሁኖ አልተገኘም። ጋዜጠኛ ደምስ እንደሚለዉ ከአርበኛዉ ጋር ኮሾሮ በልቼ ቂጣ አብስዬ የሆድ የሆዴን ተነጋግሬ ማስታወሻ ይዤ ተመልሻለሁ በተደጋጋሚ ወደ ኤርትራ ባቀናም በዛ የሚሰራዉ ስራ ጤናማ አለመሆኑ ስለገባኝ የማስጠንቀቂያ ፊሺካ አሰማለሁ በማለት ወደ ወገን እንደገና ተመልሻለሁ ብሏል። ይህ እንቅስቃሴ የግንቦት 7 ደጋፊዎችን ቢያስቆጣም ጋዜጠኛ ደምስ ደግሞ በምድረ አሜሪካ እስከኖርኩ ድረስ ህገመንግስታዊና ሰብአዊ መብቴ ስለሆነ በተሰጠኝ መብት መሰረት መብቴአነ ተግባራዊ አደርገዋለሁ በማለት በአጽንኦት ድርጊቱን ቀጠለ ።
በተመሳሳይ ሁኔታ ቀደም ባለዉ ጊዜ አቶ አበራ ለማ ሲፈርድበት አቶ አንዳርጋቸዉ በታሰረበት ማግስት ቀኑን በትክክል ሳያሰላ ቀርቶ ስለበአሉ ግርማ በማዉጣቱ የእሩምታ ተኩስ ከየአካባቢዉ ተተኩሶ ጥጉን እንዲይዝ ተደረገ።ወደ አዉሮፓ ግድም የምትኖር አንድ እህትና የሷን ሀሳብ የሚጋሩ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይነት ባለዉ ጽሁፍ አቶ አበራን አወገዙ አቶ አበራም ባልተመጣጠነ ቅጣት በገዛ ወገኖቹ ወደቀ። ተቃራኒዎቹ በሱ ብቻ ሳይወሰኑም ወደ ቤተሰቡም ተሸጋግረዉ ስለ ልጆቹ አላስፈላጊ ትችት ሰጡ። እንደዉም አንድ የግንቦት 7 አቀንቃኝ በድፍረት ስለ አቶ አንዳርጋቸዉ በቅጡ እንዳናዝን ሆን ተብሎ የተሰራ የወያኔ ሴራ ነዉ ብላ በድፍረት ጽሁፏን አወጣች። የሚገርመዉ አቶ አበራ የከሰሳቸዉ ሰዎች በህይወት እያሉ መልስ ለመስጠት ከብቃት በላይ ችሎታ እያላቸዉ የእንቅቡ መንጣጣቱ የሚገርም ነበር።
ይህች እህትና የእሷን ሀሳብ የሚጋሩ ወገኖች ያልተረዱት ነገር ቢኖር ለአቶ አንዳርጋቸዉ የድርጅቱ ሰዎችና በሱ በኩል መሽሎኪያ አናጣም ብለዉ የሚባዝኑ የሻቢያና የዘር አምላኪዎች የሚያብዱለትን ያህል ለሀገሩ ቋሚ ሀዉልት ሰርቶ እንደወጣ የቀረዉ የብእር ሰዉ፤የፖለቲካ ተንታኝ፤ምሁር፤ጋዜጠኛ፤ዲፕሎማት በአሉ ግርማ ነገር ሲያንገበግባቸዉ የሚኖሩ ዜጎች ቀላል እንዳልሆኑ እሷና መሰሎቿ ሊረዱት በተገባቸዉ ነበር። ከመጣዉ ባለጊዜ ጋር ብቻ ከመደነስ ባለፈዉ ለሀገራቸዉ ዉለታ የዋሉትን ማስታወስ ሀገር በቀጣይነት እንዲኖር ከማድረጉም በላይ ዜጎችም ለሀገር ለመዋል የተቻላቸዉን ጥረት ያደርጉ ነበር።
አንድ ታጋይ ወደ ትግል ሲገባ ከዚህ የከፉ ጉዳዮች እንደሚገጥሙት ጠንቅቆ ያዉቃል። አቶ አንዳርጋቸዉም ከድርጅት አባሎቻቸዉ ጋር የቀጥተኛ መስመር ተቋርጦባቸዉ ነዉ እንጂ ስለእኔ አታስቡ ስራችሁን ቀጥሉ ወያኔን፤ ሻቢያን የዘር ድርጅትን አትመኑ (የእኔ ህልም ነዉ ይሄኛዉ) ብለዉ ትእዛዝ የሚሰጡ ይመስለኛል ምንም እንኳን በህወአት ቴሌቨዠን ቀርበዉ የተናገሩት ሌላ ቢሆንም ።
እነዚህ በኢትዮጵያዉያን ተከልለዉ የሚያሳክሩ ጸረ አንድነት ሀይሎች ጠንከር ያለ ኢትዮጵያዊነት ሃሳብ ሊያመጣ ይችላል በሚሉት ዜጋና ጽሁፍ ላይ፤ በፓልቶክ አልፎ አልፎም በኢሳት አማካይነት ሰብአዊነት ባልተላበሰ አነጋገር ግለሰቡን በማሸማቀቅ፤በማዋከብ ከፖለቲካ ጨዋታ ዉጭ ያደርጉታል። ይህንንም ልምድ ከቅንጅት ማግስት አንስቶ ሲጠቀሙበት ተስተዉሏል ጋዜጠኛ ደምስም ጉዳዩን በስሱ ሂዶበታል። በተለይ በዚህ በተቀነባበረ የጥቃት ሰለባ ግምባር ቀደም ከሆኑት ወገኖች መሀል ዶር ታየ ወ/ሰማያት ፤ኢንጂነር ሀይሉ ሻዉል፤ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሀይሌ በተወሰነ መልኩ ኮለኔል ጎሹ እና ሌሎችም ምርጥ ኢትዮጵያዉያን ይገኙበታል። ኢንጂነር ሀይሉ ይህ ገደቡን የጣሰ ስድብ ተመጣጣኝ እንዲሆን በአንድ ቃለ መጠይቅ ከረንት አፌየርስ ለተባለዉ ለፓልቶክ ክፍል ተማጽኖዋቸዉን አቅርበዉ እንደነበር ሁላችንም የምንስታዉሰዉ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር።
ቀደም ሲል በታላቅ ኩራት የቀድሞ የፓርላማ ተመራጭ ነኝ ብሎ እራሱን ያስተዋወቀን ክቡር ኑረዲን ነዉ መሰለኝ ስሙ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ በጻፉት የምርምር ጽሁፍ አስተያየት መስጠት ፈልጎ ማጣሪያዉ ቢያጥረዉ የደብተራ ትምህርት ብሎት አጣጥሎት አልፏል። እንግዲህ ይህ ብዙ ያወቀ የመሰለዉ የቀድሞ የፓርላማ ተመራጭ ነኝ ባይ ህወአትና ሻቢያ በተካካዱበት ዉል ምክንያት በተነሳ ጦርነት 70000 የወገን ጦር እንደ ቅጠል ከረገፈ በሗላ ያስመለሱትን መሬት እንኳን ማስከበር ያልቻለ ፤አሰብና ኤርትራ ያለምንም ተቃዋሚ ከእናት አገራቸዉ ተገንጥለዉ ሲሄዱ ተቃዉሞ ያላሰማ ፤ኢትዮጵያ በዘር ተከፋፍላ ብትንትኗ ሲወጣ ደስታዉን በጭብጨባ የገለጸ ካድሬ ዛሬ ከአለም ምሁራን ጎን ተርታ የሚቀመጡትን ምሁር የደብተራ ትምህርት ብሎ ሲያጣጥል ምን ይባላል? ስንት የሚጠቅም ጽሁፍ እየተጣለ እንዲህ አይነት ዝባዝንኬስ ለአንባቢ ማቅረብ ጥቅሙ ምንድነዉ?። መቼም ስለ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሀይሌ ትልቅነት መናገር ጊዜ ማጥፋት ስለሆነ ማለፉ ይመረጣል። ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሐይሌ ምሁር ብቻ ሳይሆኑ የምሁር ደረጃ መዳቢም ናቸዉ ጀግናም ናቸዉ። ክቡር የህወአት የፓርላማ ተመራጭ ግን ይህንን ሳይመዝን በሚቀጥለዉ ጽሁፉ ደግሞ ነገሩ ሁሉ የተሳከረ የኒዎ ሊበራሊዝም ትንተና ይዞልን ቀረበ መቼም ተዉ አይባል መሀይመነቱ ገዝፎ ጠልፎ እስኪጥለዉ መመልከት ነዉ እንጂ። መለስ ዜናዊስ ፍሬ ከርስኪ 700 ገጽ ያህል ድርሳን ደጉሶ አልነበር ከሱ ጋር አብሮ በነነ እንጂ።
ይህን በዚህ ሁኔታ ካቀረብኩ በሗላ በአንባቢዎቼ እንደ መንደርደሪያ ታይቶልኝ ጋዜጠኛ ደምስ ሔኖክን አስመልክቶ ወደጻፈዉ ስመለስ። ጋዜጠኛ ደምስ ሔኖክ በአቋሙ እንደተጎሳቆለ አድርጎ አቅርቦ ከዛም ገፋ ብሎ ሄኖክ መብቱ ነዉ የሚል አስተያየትም አክሎበታል። እዚህ ላይ ሄኖክ እንደማንኛዉም ነጻ ዜጋ የራሱ የግሉ የሆነ አመለካከት ይኖረዋል ወያኔነቱንም ከመረጠ የሚነካበት የለም ፡ያለበት አገርም ይህንን ሰብአዊ መብቱን ያከብርለታል በዚያ የሚኖሩት ዜጎቹም ይህን መብቱን የማክበር ግዴታቸዉ ነዉ። ጋዜጠኛ ደምስ እራሱ እንደተናገረዉ ወያኔ ዘመም የፖለቲካ እምነቱን ለመጋፋትም ይከብዳል ምናልባትም የተሰራበትም ሊሆን ይችላልና።
ይህ እንዳለ ሁኖ የሄኖክ የግል እምነቱ የግል የማይሆንበት ጊዜም እንዳለ ማሳየት አግባብ ነዉ። ሄኖክ በጣም ጉልበታም በሆነዉ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተቀጣሪ ሰራተኛ ነዉ። ከዛ የሚያስተላልፈዉ ማንኛዉም መልእክት ሁሉ አንድ ፕሮፌሺናል ጋዜጠኛ የሚያስተላልፈዉን እንጂ የግል እምነቱን ያንጸባረቀ መረጃና ትንታኔ ሊሆን አይገባም። “እናንተ የአለም አይን ናችሁ አለም እዉነታዉን በእናንተ አይን ያያል” ተብሎ ለጋዜጠኞች መመሪያ ቢሰጥም አለም ግን በሄኖክና በአዳነች ፍስሀዬ አይን ያየዉ እዉነታዉን ነባራዊዉን ሳይሆን የነሱን ወያኔያዊ እዉነታ ነዉ። ይህን አስመልክቶ ቀደም ባለዉ ጊዜ ለቪኦኤ ስለነዚህ ሰዎች መላ እንዲፈለግ በስልክ እና በድር ጥንጥን መስመሩን ኢትዮጵያዉያን ቢያጨናንቁትም የሄኖክ ቀጣሪዎች የህዋት ቀጣሪዎች በመሆናቸዉ የህዝቡን ጩኸት ዋጋ ሳይሰጡት ቀርተዋል ሄኖክም ወያኔነቱን ቀጥሎበታል።
የተቆጣ ህዝብ ብዙ ያደርጋል የደፈረ ክራቫት ይስባል፤ ራቅ ካለበትም ጫማ ይወረዉራል፤ ከጠነከረ ደግሞ በነጎድጓድ ድምጹ መብረቅ ጥሎ ይገላግላል። ይህ ሁሉ ሲሆን ያየነዉ ቢሆንም ሄኖክ ላይ ግን ይህ ሁሉ አልተሞከረም። ሄኖክ የሚያየዉን ከወገናዊነት በጸዳ መልኩ እንደ ካሜራዉና ድምጸ መቅረጫዉ ሊያቀርብ ሲገባ እያሸና እያስተካከለ ለህወአት እንዲመች አድርጎ ካቀረበ የጋዜጠኝነት ሺፋን ሊሰጠዉ አይገባም (persona non grata)። በዚህም የተነሳ ድምጹ የታፈነ ህዝብ ሄኖክን ቢቆጣዉ ገሰጸዉ እንጂ አልተበቀለዉም ባይ ነኝ። የጋዜጠኛ ደምስ ሀሳብ ሁሉም ተስማምቶኝ እዚህ ላይ ተለይቻለሁ።
እዚህ ላይ ዉድ አንባቢዎቼ ከዚሁ ከቪኦኤ(VOA) ቤት ሳልወጣ በመለስ ዜናዊ ህወአት ትእዛዝ 280 ህጻናት በጠራራ ጸሀይ ሰላማዊ ሰለፍ ወጣችሁ ተብለዉ ሲታጨዱ አድሃነች ፍስሀዬ የተባለቸዉ የዚሁ የቪኦኤ ተቀጣሪ ምንም ሳይሰቀጥጣት የስርአቱን ደጋፊ እና ተቃዋሚ በወቅቱ ስታወያይ “እነሱም (ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ማለት ነዉ) ድንጋይ ይወረዉሩ ነበር” ያለችዉ ቪኦኤ አርካይቭ ዉስጥ ይገኛል:: የህች ሴት በቦታዉ ተገኝታ የሳሞራን ቦታ ብትይዝ ልታደርስ የምትችለዉን ጥፋት አንባቢ በአይነ ህሊናዉ ይቃኘዉ ከማለት በስተቀር ምን ማለት ይቻላል?። ጋዜጠኛ ደምስ ይህችን ሴት መብቷ ነዉ እንደማይለኝ እርግጠኛ ነኝ።
እንግዲህ የቪኦኤ ወያኔዎች ነገር ይህን ይመስላል በታንክ የታጀበ በራይት ጊር(riot gear) የታጠቀ የህወአት መንጋ ድንጋይ ለወረወሩት ህጻናት (መወርወራቸዉም እዉነት ከሆነ) የሞት ቅጣት ይፈርዱባቸዋል አሜሪካ አገር ቁጭ ብለዉ ፕሬዚዳንቱን ተኩሶ ያቆሰለ በማይገደልበት አገር። አድሀነች ፍስሀዬ ይህን ስትናገር ቀጥታ(live) ስለሆነ ተጠንቅቃ ነዉ በቤተሰብ ስብሰባ ግን ምን ልትል እንደምትችል መገመት አስቸጋሪ አይሆንም። በግሏና መሰሎቿን ሰብስባ በዛን ቀን ወያኔ ባደረገዉ ገድል ሻምፓኝ አትከፍትም ይባላል? እንግዲህ ይህን ነገር አንባቢ ይፍረደን። ይህ የእመቤት አድሀነች ፍስሀዬ የጭካኔ ስራ ግር ያለባቸዉ ዜጎች ጊዜዉም ስለራቀ ነገሩም ከአእምሮዋቸዉ ስለደበዘዘ ወደ ቪኦኤ አርካይቭ ጎራ ብለዉ በዚያን ጊዜ የተደረገዉን ቃለ መጠይቅ ጎግሎ መስማት ጠቃሚ ይሆናል እላለሁ። ነገሩን ነገር አነሳዉ እንጂ ትዝታ በላቸዉም በዚህ በተከበረዉ ወንበር ተቀምጣ ተዉ አትቆንጥጠኝ ስትል ተደምጣ ነበር። እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሲበዙ መሰለኝ እነ ሰለሞን ክፍሌም ገለል ማለት የጀመሩት።
የፕሮፌሺናሊዝም ኤቲክ( professional ethics) ሄኖክንም ሆነ አድሀነች በደምብ ሊረዱትና በመርህ ደረጃ ሊከተሉት ይገባል። ፕሬዚዳንት ሬጋን በጥይት ተመትተዉ ወደ ሆስፒታል በሄዱበት ጊዜ ቀዶ ጥገና ሊደረግላቸዉ በዝግጂት ላይ እንዳሉ ዞር ብለዉ ለመሆኑ ሪፐብሊካን ናችሁ ብለዉ ሀኪሞቹን ቢጠይቁ የቡድኑ መሪ ፈጠን ብሎ ለዛሬ ሪፐብሊካን እንሆናለን ብሎ መልሶ ነበር። ጠላታችንም ብትሆን ማዳን የሙያ ግዴታችን ነዉ ለማለት ፈልጎ መሰለኝ። ይህ ክስተት በዘር ለተለከፉት ለቪኦኤ ሙያተኞችና ሌሎችም ትምህርት ይሰጣል የሚል እምነት አለኝ።
የጋዜጠኝነት ሙያ የጠሉትን የሚቀጡበት የሚወዱትን የሚክቡበት ሳይሆን እንደ ሬጋን ሀኪሞች ስራዉን በፕሮፌሺናል ኤቲክስ (professional ethics) የሚወጡበት ሙያ ነዉ። ያ ካልሆነ ዛሬ በትችት የተጀመረዉ የህዝብ ቁጣ ነገ ወደ ሌላ ሊሸጋገር ይችላል። እዚህ ላይ የኢሳት ሰዎችም መልኩን ይለዉጥ እንጂ ከስህተት የጸዱ አይደሉም አለሙ ሁሉ በነሱ ቅኝት ብቻ እንዲደነስ ይፈልጋሉ። ኢሳት በኢትዮጵያዉያን ገንዘብ በእግሩ ቁሞ ኢትዮጵያን በእጅጉ ለሚጠሉ ግለሰቦችና ድርጂቶች ክፍት በር ሁኖ ሲያገለግል ቆይቷል እርምት ካልተደረገበት ችግር ዉስጥ እንደሚገባ ከወዲሁ በድፍረት መናገር ያስችላል።
ነገሬን ሳልጨርስ ጋዜጠኛ ደምስ ስለነ ኮለኔል ታደሰና በዛብህ ጴጥሮስ በማንሳትህ ሊያስመሰግንህ ይገባል ለመሆኑ ወደዛ ስታቀና አንተዉ እራስህ ይህን ነገር ጠይቀህ ነበር? እነዚህን ጀግኖች አስመልክተህ አንዳንድ ዘገባ ታቀርብልን ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። በዛ ያሉ አርበኞችስ ነገ የነኮለኔል ታደሰ ጽዋ እንደማይደርሳቸዉ ምን ማስተማመኛ አግኝተዋል? በዚህና ተመሳሳይ ጉዳዮች ለእኛ የራቁብንን አቀርበህ ታሳየን ይሆናል የሚል እምነት አለን።
ባጠቃለይ ነገሬን ለመዝጋት ሄኖክም ሆነ አድሀነች ሌሎችም ቪኦኤ ዉስጥ በሀወአት ጋሻ ጃግሬነት የመሸጋችሁ ሁኔታዉ እየገፋ ህዝብን መናቃቸሁ ከጨመረ ከቀጣሪዎቻችሁ ጋር በእኩልነት ሊወያዩ የሚችሉ የተከበሩ ተሰብስበዉ የተቀመጡ ወገኖች ስላሉን እነሱ ማስተካከያ እንዲሰጡበት መጠየቃችን ግድ ይላል።
ይህን ጽሁፍ እንደጨረስኩ ታሪኩ አባ ዳማ (ተናግረዉ የሚያናግሩ…. በኢትዮሚዲያ ላይ) ሚዛን በሚዛን የደምስን ጽሁፍ ከመተቸት ይልቅ ከላይ በጠቀስኩት መልኩ በማሸማቀቅ ወያኔያዊ ዜግነት ለደምስ በመስጠት መልእክቱን ዘግቶታል። ታሪኩ አባ ዳማ ምላሽ መስጠት ካለበት አሀዝ እየጠቀሰ ጦራችን ይህንን ወረዳ ተቆጣጥሯል፤ በወገን ጦር ብቻ ታግዘን ከወያኔ ግማሽ ትግራይን ሙሉ በሙሉ ጎንደርና ወልቃይትን ተረክበን በቦታዉ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያ ባንድራን አዉለብለበናል፤ የወያኔን የመሳሪያ ዲፖ ጥሰን ምርጥ መሳሪያዎችን ለወገን ጦር አድለናል ፤ያለ አግባብ በወያኔ የታሰሩ ዜጎችን ከወልቃይት፤ከጎንደር፤ከትግራይ ለቀናል፤ በሱዳን የሰፈረዉን ወራሪ ሀይልም ከወገን ጋር በመሆን በመጣበት መልስናል በህዋአት የተቸረዉ የኢትዮጵያ ግዛትም የጥንት ድምበሩን ይዟል፤ለሻቢያ ሰራዊት ዳግም አንታለልመ ተመለስ ብለናል የሚለዉ እዉነት ያዘለ መልእክት እንጂ አስመራ ሄደዉ የሞቱብንን ወገኖች በደምስ በኩል መነገሩ፤ ለጦሩ እየተባለ የሚላከዉ ገንዘብ ለኮለኔል ፍጹም ልዩ ገቢ መሆኑ መገለጹ ሊያሳስብህ አይገባም እላለሁ። ካንተ ከፖለቲካ እምነት ዉጭ መሄዱም ወያኔ የሚያደርገዉ ስላልመሰለኝ ለወያኔነቱ ማረጋገጫም ጊዜ ልንሰጠዉ ይገባል ወይም በመረጃ ብታረጋግጥልን ሚዛን የሚደፋ ይሆናል። ከዚህ በፊት ብዙ አገር ወዳዶችን አስደንብረን ለአንድነቱ ሊጠቅሙ የሚችሉትን ወደ ወያኔ ጎራ ከተናቸዋል። ይህ ወይ ከእኔ ወይ ከእኔ በተጻራሪ ወይም ደግሞ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነዉ የሚለዉ አካሄድ ኢትዮጵያን ከስልሳዎቹ ጀምሮ ሲያጠፋ እንጂ ሲያለማ ስላላየን ቆም ብለን እናስብ እላለሁ። በእርግጥ ኢትዮጵያዊ ከሆንክ ደምስ ወንድምህ እንጂ ባላጋራህ ሊሆን አይችልም ቢያንሰ ከሻቢያ በተሻለ ልታቀርበዉ ይገባ ነበር።
እንደ እዉነቱ ከሆነ እኛም እንደ እናንተ ከኤርትራዉያን ጋር ነዉ የምንኖረዉ በየቦታዉ የምንገናኘዉ ኤርትራዉያን ኢትዮጵያን አስገድዶ አሰብን ከመጠቀም ዉጭ ለኢትዮጵያ ቀና የሚያስቡ አልገጠሙንም። በኢትዮጵያ በኩል ነብሳቸዉን አድነዉ አሜሪካ እና አዉሮፓ ሲደርሱ ሲነገራቸዉ የኖረዉን ከማንጸባረቅ በስተቀር በምድር ላይ ያለዉን አዉነታ ሲቀበሉም አላየንም። ፍቅር እና ክብር ከሁለቱም አቅጣጫ ካልሆነ ሌላዉን ተዋራጂ ያደርገዋል። ስለዚህ እባካችሁ ኢትዮጵያ ነጻ የምተወጣዉ በሻቢያ መልካም ፍቃድ ነዉ የሚለዉን የተንበርካኪነት ሀሳብ ይዛችሁብን አትቅረቡ። ኢትዮጵያ 100 ሚሊዮን ህዝብ ያላት የጀግና አገር ነች ዱሩና ደኑን ህዝብችንን አድርገን ትግሉ ይቀጥል እንደዉነቱ ከሆነ በዛ በኩል የምታጠፉት ገንዘብ እና ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ዉሎ ቢሆን ዛሬ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ትገነባ ነበር። አንዴ ከዘር ድርጅት ጋር መክነፍ አንዴ ድጋፍ አገኛለሁ ብሎ የኢትዮጵያን ህዝብ በእሳት ሲያጋዩ ሲያርዱ ከነበሩ ጋር ማበዱ ዉጤቱ እንዳያችሁት ስለሆነ በተረጋጋ መንፈስ ኢትዮጵያዊ መፍትሄ ቢፈለግ መልካም ነዉ እላለሁ። እዚህ ላይ በአጽንኦት መናገር የሚቻለዉ የተሰራዉ ጥሩዉም ሆነ መጥፎዉ ተመዝግቦ ተቀምጧል ዳግም ስህተት ላለመስራት መጠንቀቅ ተገቢ ነዉ እላለሁ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ሰመረ አለሙ
Ato Abera Lema is coming again using another false name. I do not know why he uses so many differenet names to spread his poison and pro-weyanne propaganda. He can not escape or avoid the radars of Ethiopians and it has been easy to find and catch him in the cyber space. Welcome back ato Abera Lema and have the courage to use your own name.
ጣልያን በሀገራችን የተወው ነገር ቢኖር ባንዳነትንና ሽርሙጥናን ነው።
የዚህ ፅሁፍ አቅራቢም ባንዳ ብቻም ሳይሆን አደርባይ ጭምር ነው።
በአንድ እራስ ሁለት ምላስ ይሉሀል እንደሰንተ አይነቱን ነው።
እዚህ ጋ ደምስ ያለአግባብ ወያኔ መባሉ አሳዝኖሀል።ወዲህ ደግሞ አንተው ራስህ ሰዎችን ወያኔ በማለት ትፈርጃለህ።
በዚህ ጉዳይ የፈለጋችሁትን በሉ እኔን የሚያበሳጨኝ ነገር የሰውን ድካም ከንቱ ለማድረግ የምትሄዱበት መንገድ ነው።
ለወያኔስ ለምን እድሜ ትሆኑታላችሁ?
ሁሉም በመሰለው ይታገል።አንተም በመሰለህ ታገል።የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው እንደተባለው በዛም ሆነ በዚህ እኛ የምንፈልገው ነፃነትን የሚያመጣልንን ነው።
አንተ ለነፃነት አስተዋፅኦ የምታደርገው ብዕርን ከወረቀት በማዋሀድ ትችትን ነው ሌሎች ግን ዳግም የማያገኝዋትን ህይወታቸውን ጭምር ስለሆነ ተዋቸው።ታጋዮችን ስማቸውን እያነሳችሁ በስቅታ አትግደሉዋቸው። ባንዳ ሁሉ።
አቶ ሰመረ ላገራቸው ብሄራዊ ጉዳይና ነጻነት (ከሻቢያና ከወያኔ ተጽእኖ ውጭ) ስለሚያስቡና ስለሚጽፉ ሰዎች ጥቃት በመጻፍዎ ይመሰገናሉ፡፡ ግብረ በላዎች ደራሲ አበራ ለማን፣ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠን፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌን፣ ጋዜ7ጠኛ አበበ በለውን ወዘተ… ሁሉ በየተራ ዘምተውባቸዋል፡፡ የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ እንዲሉ፣ ወያኔንና ሻቢያን ትተው በነጻነትበሚያስቡና በሚጽፉ ጀግኖች ላይ ሲደነፉ ይታያሉ፡፡ አቶ ሰመረ ካነሷቸው ሁለት የሻቢያና የወያኔ ምንደኛ ጸሃፊዎች መካከል ካውሮፓ የምትጽፍ እህት ያሉዋትና ( ግርማ እንድርያስ ሙላት aka አዜብ ጌታቸው) ታሪኩ አባዳማ (ሙሉጌታ ዘውዴ ድልነሳሁ) ይገኙባቸዋል፡፡ ግርማ እንድርያስ ባደገኛ እጽዋት ሱስ የተለከፈና የእድሜውን ግማሽ በአእምሮ ሕመምተኞች በሆስፒታል እያሳለፈ ያለ መናኛ ሰው ነው፡፡ ማንም ሰው ጫት፣ እጹንና አረቄ ከገዛለት የማይም ብእሩን አንስቶ በግለሰቦች ላይ የሚዘምት መሆኑን ከኔዘርላንድ የተገኘው ማስረጃ ያረጋግጣል፡፡
ታሪኩ አባዳማ aka ሙሉጌታ ዘውዴ ድልነሳሁም እንደ ግርማ እንድርያስ ሁሉ ለሌሎች ጸረ አንድነት ኃይሎችና ግለሰቦች እየተገዛ በግለሰቦች ላይ የሚዘምት የቀይ ሽብር ወንጀለኛ ነው፡፡ ይህ በካናዳ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ በቀድሞው የጨቦና ጉራጌ አውራጃ ውስጥ ዋና ካድሬ በነበረበት ጊዜ ብዙ ሰዎችን በቀይ ሽብር የጨረሰና ቤለበረት የ18 ዓመት እስራት ተፈርዶበት የሚፈለግ ወንጀለኛ ነው፡፡ እዚህ አብሮን በሚኖርበትም አገር በራሱ እውነተኛ ስም ከመጠራት ተቆጥቦና ከህዝብ ርቆ እየተሸማቀቀ የሚኖር ከንቱ ሰው ነው፡፡ እነጋዜጠኛ ደምስ ላይ ቢጽፍ አይፈረድበትም፡፡ እነሱ ደፍረው ያነሱትን የሻቢያን መሰሪነት እነ ሙሉጌታ ዘውዴ ደፍረው ሊያነሱና አለቆቻቸውን ሊያስቀይሙ አይፈልጉምና!!!
እውነቱ በለጠ
Thank you Ewnetu. I wonder why website owners give a chance for such criminals like Mulugeta Zewde when they come up with their undercover names like Tariku Aba Dama. If they are courougeous let them come up with their real name.
ቀሲሱ ሼክስፒር ፤ ከቅኔው መሃል
መጽሃፈ ሻይሎክን ፤ ወልደ ዶንኪዮቴን
አገኘው ሲያብል፤
“ሰውን ብሉ! ብሉ!… ሰውን ቀቅላችሁ
ጥብስና ብርንዶ ፤ ሲሻችሁ ሲያምራችሁ
ወዳጁ መስላችሁ ፤ ከጓዳው ገብታችሁ
ቤቱን አጣርሳችሁ ፤ ጣሪያውን ነድላችሁ
ሰውን ብሉ ! ብሉ!… ሥጋውን ነጭታችሁ
ደሙን ጠጥታችህ ፤ ሕይወቱን ሠርቃችሁ
በሬ ወለድ ዜና፣ ባሽከር በትናችሁ
ሌት ተቀን ድከሙ፣ ካብ አይገቤን ሁላ እያቃቄላችሁ ”
እያለ ይሰብካል ፤ ሻይሎክ ወልደ ጢዮር
ሃሜትና ተንኮል ፤ ሲሸርብ ሲደምር፤
ቀሲሱ ሼክስፒር ፤ ከቅኔው መሃል
መጽሃፈ ሻይሎክን ፤ ወልደ ዶንኪዮቴን
አገኘው ሲያብል፤
መጽሃፈ ሻይሎክን ፤ ያነበበ ሁሉ
ንጹህ ልቡን ሰጥቶ ፤ ሸፍጥን መቀበሉ
አይቀሬ ነውና ፤ ታመሰ አገሩ
ባሉባልታ ፈረስ ፤ ታሰሰ ሰፈሩ
መጽሃፈ ሻይሎክን ፤ ሃጂ ቱልቱሌን
ቄስ አባወናፌን ፤ ይሉኝታ ምኔን
ተስር ላስተዋለው ፤ ለመረመረው
ባድርባይነቱ ባጨብጫቢነቱ ወደርም የለው
ዛሬ ካንተ ጋራ ፤ ነገ ተሱ ነው፤
ቀሲሱ ሼክስፒር ፤ ከቅኔው መሃል
መጽሃፈ ሻይሎክን ፤ ወልደ ዶንኪዮቴን
አገኘው ሲያብል፤
አራት መንግሥት በልቶ ፤ ዛሬም ይቋምጣል
ሞኝ ባገኝ እያለ ፤ ሰው በሰው ይድጣል
ሻይሎክ ዶን ኪዮቴ ፤ የማንቻው መንጣጋ
ታየሩ ተባዶው ፤ ሲጣላ ሲላጋ
ተራሱ ተጣልቶ ፤ ተራሱ ተቧቅሶ
እራሱን በራሱ ፤ አሸንፎ ጥሶ
እዩት ሲንጠራወዝ ፤ በዶንኪዮትኛ
መርዙን እየረጨ ፤ ይመስላል ቤተኛ፤
ምስኪን ወዳጆቹ ፤ አልነቅተውን ገና
ለላላው ብሎኑ ፤ ማጥበቂያ ካቴና
መልቲ ቀጣፊነት፣ ሰጥተውታልና!
ቀሲሱ ሼክስፒር ፤ ከቅኔው መሃል
መጽሃፈ ሻይሎክን ፤ ወልደ ዶንኪዮቴን
አገኘው ሲያብል፤
መጽሃፈ ሻይሎክን ፤ አንብቦ የለየ
ወልደ ዶንኪዮቴን ፤ አሳምሮ ያየ
ሰው ማለት ምንድነው? ማንስ ነው ምንትስ?
ብሎ መመራመር ፤ አይሻም በጭራሽ፤
በገሃድ ያየዋል ፤ እኩዩን ቦዘኔ
ካብ አይገቤ ሁላን ፤ አገር ሻጭ መደዴ፤
ምላስ አገር ቆላ ፤ ምላስ ወገን በላ
ጨዋነት ተነውሮ ፤ ብልግና ተኮላ፤
ዘረኝነት ፋፍቶ ፤ ጎጠኝነት ፋፍቶ
ያገር ቤቱ ብቅል ፤ እዚህ ተመንድጎ
ላዳል ሞቲ ምሱ ፤ ሻይሎክ ደም ተጠማ
ወሬ አይደበቅም፣ ማበዱ ተስማ፣
ግብር ገብሩለት ፤ ማተቡን በጥሷል
ታላሀ እንዲታረቅ፣ ምህላ ተይዟል፤
ቀሲሱ ሼክስፒር ፤ ከቅኔው መሃል
መጽሃፈ ሻይሎክን ፤ ወልደ ዶንኪዮቴን
አገኘው ሲያብል፤
“ሰውን ብሉ! ብሉ!… ሰውን ቀቅላችሁ
ጥብስና ብርንዶ ፤ ሲሻችሁ አምሯቸሁ
ወዳጁ መስላችሁ ፤ ከጓዳው ገብታችሁ
ቤቱን አጣርሳችሁ ፤ ጣሪያውን ነድላችሁ
ሰውን ብሉ ! ብሉ!… ሥጋውን ነጭታችሁ
ደሙን ጠጥታችህ ፤ ሕይወቱን ሠርቃችሁ
በሬ ወለድ ዜና፣ ባሽከር በትናችሁ
ሌት ተቀን ድከሙ፣ ካብ አይገቤን ሁላ እያቃቄላችሁ ”
እያለ ይሰብካል ፤ ሻይሎክ ወልደ ጢዮር
ሃሜትና ተንኮል ፤ ሲሸርብ ሲደምር፤
ቀሲሱ ሼክስፒር ፤ ከቅኔው መሃል
መጽሃፈ ሻይሎክን ፤ ወልደ ዶንኪዮቴን
አገኘው ሲያብል፤
ይሄ ሃይለኛ ግጥም አጭበርባሪውን የሻቢያ አሽከርና የወያኔ ምንደኛ የሱፍ ያሲንን ይመለከታል!…ቅቀቅቀቅ!… አስተዋዩ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እሳት ላይ በቅርቡ እንዳስገባለት ሁሉ ይሄም ገጣሚ ደህና አድርጎ አስገብቶለታል
ምነው:ጋሼ:አበራ:ለማ!!
በስተርጅና:በ70 እድሜህ:እራስህን ለወያኔ:በርካሽ:ሸጠህ:ወያኔ:ፍርሐትና:ስጋት:ስይዘው:በተቃዋሚ:ሃይሎች ላይ: ያስጮህሃል። ያሳዝናል:ያሳፍራል:የወያኔ:ቅጥረኛ መሆንህ::
I am also sorry for gashe Abera Lema. When I met him in Addis Ababa,I advised him to move out of Norway(OSLO)and totally live in Ethiopia. The anti-TPLF groups in Oslo suspect that he works for the weyanne junta and are isolating him. There are talks that the anti-TPLF groups are asking the Norwegian government to take back his citizenship and send him back to Ethiopia. He has problems in Oslo but he attacks the opposition. He is smart. He do not attack the weyanne junta. His pen and writing is only against the opposition and has many enemies in Oslo. Every body in Oslo say that he is working for the weyanne junta. But I continue to tell him to live in Ethiopia.
Extreme and radical Amhara groups in Oslo send false information about ato Abera Lema. They say he is TPLF and Hodam. I know that he does not support the TPLF and loves his country and people very much. The Oslo groups are the followers of Shabia and do not like him. But he has the truth and should not be afraid and use his own name to write and expose them, the Shabia followers in Oslo.
ኣቶ ኣበራ ለማ የሚያስቅ ፍጡር ነው።ለምን?ለምን ማለት ጥሩ ነው። እራሱ በብዕር ስም ለመጻፍ ይሞክርና ነገር ግን የብዕር ስም ለመስጠት ያነሳሳው ምክንያት ግራ ግብት ይለኛል። ምክንያቱም ኣቶ ኣበራን የሚያውቅ ሰው ንግግሩንና ጽሁፉን መለየት ኣይቻልም። ለምሳሌ ኣዳነች ፍስሃዬ ከኣፉ የማትጠፋ ነች። ሁሌ ያነሳታል በኣፉም በብዕሩም። ኣዳነች ፍስሃዬ በኣጋጣሚ ብትሞት (ኣያርግባትና) ቀብሩዋ ላይ ተገኝቶ ግጥም በመጻፍ የሚያነበው ኣቶ ኣበራ ኣይደለም የሚለኝ ካለ ዛሬውኑ ከምላሴ የተጎነጎነ ጸጉር እነቅላለሁ።
፩ ለምን?
ታዋቂው የብዕር ሰው ሃይሉ ገብረ ዮሃንስን ( ገሞራውን) የማታውቁ የላችሁም። ታዲያ ገሞራው በህይወት በነበሩበት ጊዜ ጎረበት ስዊድን እየኖሩ በስካንዲኒቪያ ውስጥ በፍርድ ቤት የተደረገባቸውንም ሁኔታ ሃገር ቤት በሚታተም መጽሔት ገልጸው ነበር። በዚያን ወቅት ከማንም በፊት ቢያንስ ስንጥፍ ኖረናል የሚሉት እነ ደራሲ ኣበራ ለማ ነበር ገሞራውን ኣለንልህ ማለት የሚገባቸው። በዚያን ወቅት ኣቶ ኣበራ ለማ ገሞራው ለየለት ይሄ ዕብድ እያለ ያወራ ነበር። ብዙዎቻችን እየታዘብን ኣቶ ኣበራን እንሰማው ነበር። የሚገርመው ነፍሳቸውን ይማረውና ገሞራው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ኣቶ ኣበራ ለማ ነበር ግጥም ጽፎ በስፍራው የተገኘው። ኣቶ ኣበራ ሰው ሲሞትለት ደስ ይለዋል። የዳንቴል ግጥሙን ይዞ ይዞራል። በስተርጅና እናት ሃገር በወያኔ እየደማች መዝሙሩ ሻቢያ….ሻቢያ እና ሰው እንደኩዋስ ሲጠልዝ መዋል ነው። ኣሁን ስማቸውን ያነሳቸው ሰዎች በጠቅላላ ቢሞቱ (ይቅርታ ወንድሞቼና እህቶቼ እኔ ስላልኩኝ ኣትሞቱም ለጨዋታው ነው) ነገር ግን ኣቶ ኣበራ ለማ በሞታችሁ ማግስት እያወደሰ ግጥም ይጽፍላችኃልም ያነበዋልም።
በሚቀጥለው ጽሁፌ ደራሲና ጋዜጠኛ ኣበራ ለማ የነማን ለቅሶ ላይ ግጥም ኣነበቡ? ሰዎቹ በህይወት እያሉ በኣቶ ኣበራ ለማ የተሰጣቸው ሜዳሊያ ምን ነበር። ኣቶ ኣበራ ለማ ኣንድ ዓይነት ኣረፍተ ነገር ለምንድን በተለየየ የብዕር ስም ይጠቀማሉ? ይቀጥላል
ኮሜንቶቹን የሞላቸው ኣበራ ለማ ነው በተለያየ የቁጩ ስሞች,,,,, ኣበራ ክፉ ነህ:-) 🙂 🙂 ሳቃችንን ጨረስክብን…..
ሰመረ አለሙ says: ኣበራ ለማ
Tsehay says: ኣበራ ለማ
[email protected] says: ኣበራ ለማ
Yitagessu says:ኣበራ ለማ
Gashe Abera is a good person and helping his country with his profession. He goes to Ethiopia many times and helps journalists
and writers. When he is in Ethiopia, he meets the EPRDF government officials and has good relations with them. He is not the extreme Diaspora that hate everything the EPRDF government works in Ethiopia. I attended one meeting in Ethiopia with Gashe Abera and he criticised the extreme and negative Diaspora members. He says the EPRDF government is doing good and the Diaspora must support the development work in Ethiopia. He does not like the anti-peace, anti-development, extreme and violent Ginbot7 group. In Oslo these extreme groups attack and hate him and say that he is the agent of the EPRDF government. I know he gets small money in Ethiopia and likes his country.
Gashe Abera Lema has written another comment using the false name `Worku Assefa Dr.`on Ethiomedia.com. He uses the Amharic name `Gimbot7` or the boot with bad smell in English to show how he hates the Ginbot7 movement. The weyanne people and supporters also use the same word `Gimbot7`when they attack the movement. Before, I resepcted the Old man gashe Abera Lema but now I believe he is working for the weyanne government. The weyanne government is spending much money and has recruited paid persons (non-Tigraways)in the Diaspora spy and attack the Ginbot7 movement. That is why Gashe Abera Lema is opening a war in the cyberspace with different false names.
Abera Lema is seen in Ethiopia(Finfine)many times with the TPLF persons.He moved from another Norwegian town to Oslo to do the assignments of the TPLF. We the anti-TPLF opposition in Oslo know all the TPLF and Hodams who go to Ethiopia and have condomiums and other small businesses. Ato Abera Lema has no employment in Norway or Oslo but goes to Ethiopia many times in one year. The source of money for his travels to Ethiopia can be the TPLF Diaspora department in Finfine.
Shame to Gashe Abera Lema. Many say he is hodam and works for the TPLF. It is true. He is writing bad things about the opposition with different false names.