የኦሮሞ ጥናት ማህበር ዓመታዊ ስብሰባ በዋሽንግተን
ኦሮሞ ጥናት ማህበር ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በዋሽንግተን ሀዋርድ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ ስብሰባውን አካሄደ። ከተያዩ ሃገራት የሄዱ የኦሮሞ እና ኦሮሞ ያልሆኑ ምሁራን በዚሁ ስብሰባ ላይ ጥናታዊ ጽሑፎቻቸውን አቅርበዋል። ጥናቶቹ በኦሮሞ ህዝብ ባህል፣ አኗኗር፣ እንዲሁም፣ በማህበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ነበሩ። በስብሰባው ከተገኙት በርካታ እንግዶች መካከል በኢትዮጵያ ከጥቂት ጊዜ በፊት ከእስራት የተለቀቁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር አቶ በቀለ ገርባ እና እውቁ የአፍሪቃ ቀንድ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጆን ማርካኪስ ዋነኞቹ ነበሩ። Listen