የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋር ዛሬ ያወያያል፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ በሚኒስቴሩ እና በሚኒስትሩ ስም ያስፈራራሉ

 

addis ababa sunday schools demo to the dioseces HQ

  • በፀረ ሙስና፣ በመልካም አስተዳደርና በዕቅበተ እምነት ንቅናቄውየአማሳኞች የሕግ ተጠያቂነት እንዲኹም በእስር እና በወከባ የሚያደርሱት እንግልት ዋነኛ ትኩረት እንደሚኾን ተጠቁሟል
  • ዋና ሥራ አስኪያጁ÷ በአለቆች፣ በካህናትና በሰባክያነ ወንጌል ላይ እንዳደረጉት ኹሉችግሮችን ውጫዊ በሚያደርግ ኦሬንቴሽን የውይይቱን ትኩረት ለማስቀየስ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም
  • ‹‹የተሾምኩት በመንግሥት ትእዛዝ ነው የሚሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ጥያቄ እና ተቃውሞ የሚያነሡባቸውን ሠራተኞች በሚኒስቴሩ እና በሚኒስትሩ ስም ያስፈራራሉ

*        *        *

  • ‹‹…የሔዱትን[በቀደሙት ውይይቶች የተሳተፉትን አለቆች፣ ካህናት እና ሰባክያን] ጠይቁ፤ ሰሞኑን ሚኒስትሩ አቅፈውኝ ትከሻዬን እየመቱኝ፣ በርታ፤ እኔ ከጎንህ ነኝ፤ ያለምንም ስጋት መንጥራቸው ብለው መመሪያ ሰጥተውኛል … ስም እየጠሩ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እስካለ ድረስ እጨርሳችኋለኹ ብለዋል፡፡ መንግሥት እርሳቸው እንደሚሉት የእርሳቸው ብቻ አይደለም፡፡ እኛ መንግሥት ከዜጎቹ ጋር ነው ያለው ነው የምንለው፡፡ ስለዚህ በአስቸኳይ ይድረስልን፡፡››

/በጥቅመኝነት እና በጎጠኝነት ትስስር ላይ በተመሠረተው የዋና ሥራ አስኪያጁ የዝውውር አሠራር የተማረሩ ሠራተኞች አቤቱታ/