የግንቦት ሰባት የሃሰት ጦርነት

ከኤሊያስ ክፍሌ (ትርጉም በ አንባቢ)

ግንቦት ሰባት በወያኔ ፋሺስት ሁንታ ላይ ወታደራዊ ድል እየተቀናጀሁ ነው በማለት በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሃገር ወዳዱንና የድርጅቱን ደጋፊዎች ለማጭበርበር እና አምታቶ ገንዘብ ለመሰብሰብ፣ እንዲሁም ሕዝብ እየተገደለ እየታሰረ ለምን ዝም ይባላል? ምን እየሰራቹ ነው? ያላቸውን የአባላቶች ቁጣ አረጋግቶ ገንዘብ ለመሰብሰብ አሰፍስፎ በወያኔ ላይ ጦርነት አወጅኩ፣ ፊሽካ ነፋሁ፣ በሚል ሰበብ በዲያስፖራው ኪስ ላይ የብዝበዛ ጦርነት ለማካሄድ የተቀናበረ ፕሮፓጋንዳ ነው። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አስፈላጊ የተባሉ መረጃዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ይቀርባል።

ላለፉት በርካታ ወራቶች በወልቃይት ጠገዴ ገበሬዎች እና በወያኔ ሚሊሻ መካከል በሰሜን ኢትዮጵያ በሁመራ ዙሪያ የተኮስ ልውውጦች እና ተደጋጋሚ ግጭቶች እንደተከሰቱ ሲታወቅ አሁን ድረስ አከባቢው በውጥረት ነው። አልፎ አልፎ የተለመዱ የቶክስ ልውውጦች ይደረጋሉ። በወያኔ ሰራዊት የሚደገፉ ሰሊጥ አምራች ነጋዴዎች በሃይል ዘልቀው የአከባቢውን ገበሬዎች ከመሬታቸው በገፏቸው ቁጥር የቶክስ ልውውጦች በአከባቢው ይሰማሉ። ይህም የተለመደ እና አሁንም ያለ ውጥረት ነው። ከተለያዩ የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች የተሰበሰበው መረጃ እንደጠቆመው በዳንሻ እና በሁመራ አከባቢ የሚገኙ ሰፋፊ ለም መሬቶች የአከባቢውን ገበሬዎች በማስገደድ በማፈናቀል እንዲሁም በምእራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል የተፈጸመው አይነት ተመሳሳይ የመሬት ቅርሚያ በማድረግና በተለያየ ዘዴ መሬቶቹን የሕወሓት ነጋዴዎች ወስደዋል። የወያኔው ስርአት በተጨማሪ በቀሪ ገበሬዎች ላይ ከፍተኛ ግብር በመጫን አከባቢውን እንዲለቁ ያደርጋል። የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ በሃይል ማፈናቀል አከባቢውን በትግሪኛ ተናጋሪዎች በማስወረር ማንኛውም ጉዳዮች ስብሰባን ጨምሮ በትግሪኛ እንዲደረጉ ጫና በመፍጠር ሕዝቡ እንዲያምጽ አድርጎታል። ይህ ጭቆና ያንገፈገፈው የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ወያኔ የዘር ማጽዳት ዘመቻ እንደከፈተበት ስላመነ በትጥቅ ትግል ገጥሞት ይገኛል። ይህንን የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ትግል የግንቦት ሰባት ድርጅት የራሱ ወታደራዊ እርምጃ አድርጎ በመሳል ሻእቢያ በሚሰራው ፕሮፓጋንዳ በጣት የሚቆጠሩ የግንቦት ሰባት ታጋዮች እንዳደረጉት አድርጎ ውዥንብር በመፍጠር በሃሰት የገቢ ማሰባሰቢያ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

የጦርነት ዜናው በኢሳት አንደተሰራጨ በማግስቱ ወያኔ አስተባብሎ ነበር፣ ሆኖም ወያኔ ሪፖርቱን እንደ ፖለቲካ ሽፋን በመጠቀም ከወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ጋር ያለውን ግጭት ለመሸፋፈን ወያኔ ከኤርትራ መንግስት ጋር እንደተጋጨ አድርጎ ለማቅረብ የፖለቲካ ስራ ሰርቶበታል። ግጭት ነበረባቸው በተባሉ ቦታዎች ቤተሰቦቻቸው ካሉ ከበርካታ ኢትዮጵያውያን በቃልመጠይቅ የሰበሰብኩት መረጃ እንደሚያመለክተው ከሁለት ግለሰቦች ውጪ በርካታዎቹ የሚሉት በአካባቢው ያለው ግጭት በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብና በወያኔ መካከል አንጂ የግንቦት ሰባት ወታደራዊ አንቅስቃሴ አለመሆኑን አረጋግጠዋል። የግንቦት ሰባት ወታደራዊ እንቅስቃሴ በወልቃይት ጠገዴ አከባቢ መኖር አለመኖሩን የጠየኩት አንድ ሌላ የአካባቢው ተወላጅ በጥያቄዬ ከት ብሎ ክሳቀ በኋላ ሀሰት መሆኑን ገልጾልኛል። የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በአሁን ሰአት ክንዱን አስተባብሮ በመነሳቱ ወያኔ የግንቦት ሰባት-ሻአቢያን ጥቃት ለመመከት በሚል የፖለቲካ ሽፋን ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል ህዝቡ ላይ እንዳይፈጸምበት ፍርሃት እንዳደረበት ግለሰቡ ጨምሮ ገልጿል።

በቅርቡ ተዋሃድን ያለው አርበኞች ግንቦት ሰባት 100 የማይሞሉ ተዋጊዎችን በኤርትራ ውስጥ ይኖሩታል ተብሎ ይገመታል። ማንኛውንም አይነት ወታደራዊ ኦፕሬሽን መፈጸም የማይችሉ እጅግ በበሽታ እየተጠቁ ያሉ እና በውሃ ወለድ በሽታ እና በወባ እየተሰቃዩ መድሃኒት ለማግኘት የማይችሉበት ደረጃ ላይ ሲገኙ ሻእቢያ የሚንከባከባቸውን የትግራዩን ደምሕት ታጋዮች ፎቶ እና ቪድዮ እያሳየ ሊያጭበረብር ይሞክራል። ሻእቢያ እና ግንቦት ሰባት ዋጋው በሳንቲም የሚገመት የውሃ ማጣሪያ ክኒኖችን እንኳን ለተዋጊዎቹ ለማቅረብ ፈቃደኞች አይደሉም። ግንቦት ሰባት የታጋዮቼ ናቸው ብሎ የሚያቀርባቸው ቪድዮዎች እና ምስሎች በደንብ ሰልጥነው እንክብካቤ የሚደረግላቸውን የዴምሕት (የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራቲክ እንቅስቃሴ) ተዋጊዎችን ሲሆኑ እነዚህ የዴምሕት ታጋዮችን ከማንም በተለየ ከሻእቢያ አትኩሮት የሚሰጣቸው መሆናቸው አስመራ ካሉ ምንጮች ለማረጋገጥ ተችሏል።

ግንቦት ሰባት ያላደረገውን አደረኩ ሲል ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ለምሳሌ ያህል በ2009 በወያኔ መንግስት ላይ ያመጹ ወታደራዊ መኮንኖች የሞከሩትን የመፈንቅለ መንግስት ያቀናበርኩት እኔ ነኝ በማለት ግንቦት ሰባት ሊያጭበረብር ፈልጎ ነበር። በወቅቱ ወታደራዊ መኮንኖቹ በሰራዊቱ ውስጥ በወያኔ የተገነባውና የተስፋፋው የዘረኝነት ድርጊት እና የጎሳ አካሄድ አንገብግቧቸው ስርዓቱን ለመናድ ተነስተው እንደነበር በጊዜው አምልጠው የነበሩ የአመጹ ተባባሪዎች ተናግረዋል። አምልጠው ወደ እርትራ የገቡት እንደ ኮሎኔል አለበል አማረ የመሳሰሉት በመፈንቅለ መንግስቱ ተሳታፊ የነበሩት ማንኛውም ወታደራዊ መኮንኖች ከግንቦት ሰባት በሙከራው ውስጥ ምንም ሚና እንዳልነበረው ይመሰክራሉ።

አርበኦች ግንቦት ሰባት እና ፈብራኪው ሻእቢያ የተለያዩ የሃሰት ዜናዎችን በመፍጠር ወታደራዊ ግጭቶች ተደርገው ድሎች እንደተገኙ በመደስኮር ከተለያዩ በዲያስፖራው ዘንድ ካሉ በወያኔ ድርጊቶች ከተማረሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ኪስ ገንዘብ ለመመንተፍ እየተራወጡ ሲሆን የግንቦት ሰባት የገቢ ማሰባሰቢያ የስብሰባ ወራቶች ሲደርስ ይህንን የሃሰት ዜና መፈብረክ ግዴታ ስለሆነ እንዲሰራጭ የተደረገ ሲሆን ምን ያህል በተቃዋሚ ሃይሎች ጎራ ውስጥ የሻእቢያ ተጽእኖ እያረፈ እንደሚገኝ በገሃድ እየታየ ነው::

የሚሰበሰበው ገንዘብ ኤርትራ ለሚገኙት የግንቦት ሰባት ተዋጊዎች የሚሄድ ቢሆን ኖሮ የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን አይቶ እንዳላየ ማለፍ ይቻል ይሆናል። ግን ጉዳዩ ይህ አይደለም። ገንዘቡ በበርሃ ላሉት ለተዋጊዎቹ አይደርስም። ላለፉት 3 ወራት ብቻ አርብኞች ግንቦት ሰባት ከአውሮፓ እና አውስትራሊያ ከሰበሰበው 200 ሺህ ዶላር በኤርትራ ለሚገኙ ለተባሉት ለታረዙና ለሚሰቃዩ ታጋዮች አንድም ፍሬ መድሃኒት፣ ምግብ እና የተለያዩ አቅርቦቶች መግዣ አልዋለም። ከዳያስፖራ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በመዋጮ የሚገኘው ገንዘብ በአውሮፓ እና አሜሪካ ለሚገኙ የግንቦት ሰባት አመራሮች ደሞዝና የጉዞ መሸፈኛ (በአሜሪካ እና አውሮፓ ከተሞች ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች ውስጥ ማረፊያ) ወጪ እንደሚውል ይታወቃል። በትግል ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ ለትግል ሳይሆን ለግንቦት ሰባት መሪዎች ምቾትና ድሎት ላይ ይውላል ማለት ነው። ከነዚህ ወጪዎች የተረፈው ገንዘብ በኤርትራ ለሚገኙ ታጋዮች ለምግብ፣ ለቫይታሚንና ለመድሃኒት መግዣ አንዲውል ቢደረግ ዝም ማለት ይቻል ነበር። ግን ይህ እየተደረገ አይደለም ሲሉ የደርጅቱ የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።

በሚቀጥለው ጽሁፍ የአርበኞች ግንባርን እና የግንቦት ሰባትን እየተፍረከረከ ያለ ውህደት እና የፖለቲካ አሻጥሮችን እንዳስሳለን።

21 Comments on “የግንቦት ሰባት የሃሰት ጦርነት”

  1. Hi what personality do u have ?i really concerned about ur mental status u always spread false propaganda ageist true opposition groups what is ur mission???????

  2. Hi Elias, I think recently you stopped to take your medication for depression. Do you think anyone believes your elusion? May be you are paid well by woyane. Try another lie

  3. Elias ante woyane yetekawamiwochin(opposition party)ewuneta enditasitebabill endemikefiluh bedenib awokehu.I have family they live around North Gonder at the border of Tigray.They told me real war b/n Ginbot 7 and woyane,so don’t spend your time.every body knows there is real war.
    ante zare washiteh gin woyane nege yamene endehone gudih fella.ahunim ale lemalet dar dar eyale new.
    Le akababiw gebere new ende yan hahil soldiers wode akababiw ye miyaguzew? tigermaleh,Banda

  4. በጣም ነው ያሳከኝ የኢትዮጵያን ህዝብ ከእንግዲህ ይታለላሉ ብለህ አታስብ አንተ የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳ ነህ የፍርሃት እና ምኞትህን ነው የምታወራው እውነቱን ማወቅ ከፈለግህ ግን ከባንዳ እና ከሆዳም በስተቀር ንፁህ ህዝብ አገሩን የሚወድ ወያኔን ያጠፋል ሌላው ቢቀር በሆዱ የተገዛውእንኴ ወያኔን ከማጥፋት አይመለስም ጊዚያት ነው የሚጠብቀው ገንዘባችሁን ሊበሉ ነው ላልከው አታስብ ይልቁንም አንድ ነገር ልምከርህ ወያኔ የሚቀልባቸው ባንዳዋቹ እነእንኳንየማውቃቸው ስማቸውን ከፈለክ ሀጒስ ፣ ክብሮምን ፣ሀዳስ ፣ ፍሰሃ ፣መሀሪ…እነሱን ተጠንቀቅ በተረፈ እውነቱን አንተው ታውቃለህ ምት ለወያኔ ኢትዮጵያ ለዘልአለም ትኑር

  5. We all new what is going on with G7 (Arbegochi ginbar) what i want to know is why Elias took you so long to confiront this fact??? you used to be up front when it comes the TRUTH. This so called G7 works with woyane’s Tags to discorege the diaspora from helping the true oppostions by misleading wrong informaton through ESAT. Shabeya by no means attemptes to truly help the so called Arbegochi ginbar to fight on the border off Erteria. The so called G7 is a bogus mafia group agreed with a Shabea embassy’s officals in washington DC to use the ESAT meadia to scam $$$$ from Diaspora around the world. No money for Shabia, G7(arbegoche) or ESAT!! We will find a way to fight woyane! Keep your hard working $ money close to your pockets my fellow Ethiopians! The 6 gungs (groups of guys) in Diaspora creat a business venture to make money by selling false propaganda through ESAT. To mention some of the pepoples Dr. Berhanu’s sister, the erteran’s blood ties Dr. Aziz (claims born and raised in Wollo) the former Dr Berhanu nega’s sister boy frined. also Mulegeta Lule esat’s news room guy, of course the biggest fundraiser scum Tamage Beyen (Lemage Beyene)etc. How could we fall the propaganda of So called Berahnu nega the last 9 years??? yes his gung’s use to say “Berhanu has a lots of money does not needs Esat or G7 money” the Hailu shawel’s gangs they used to tell us the same thing untill we found out he basiclly keept the money we sent from diaspora to his account. Now look where he is? That is so sad story, they run business on the expenseses of our people.

  6. Hi! Elias u already join the hodam camp of Solomon Tekalign. Congra, How much is ur share from Weyane frifari? Don’t worry, we believe 100% our freedom fighters and will support them what ever we can. At final end of the Rule of Weyane we and our freedom fighters Including our favorite Shaebia will celebrate at Mesqel Square, Addis Ababa.

  7. Elias forget this G7 gangsters and keep doing the right thing. You have been writing about weyane most of your life. In fact when Boss Birhanu was in bed with weyane you were against weyane who have the moral authority to label you what ever they think you are?

  8. Elias, are you mad? are you woyane cadere? I am sure you are an agent of TPLF. We do not hear you. you are a Pathological liar, a Compulsive liar, a Chronic liar, and a Habitual Liar. It is very surprising. if you want to know the fact, you can go the hero fighting field. I do not think you can go because you are coward.Stop your pretext reason.

  9. Elias has the right to tell the truth about Woyane/ shabiya. leave him alone. The toxic diasporas are barking like a dog/ goat/ cat.

  10. ኤልያስ ክፍሌ የምትራመድ በትን ምድር አስውለህ ለማየት ያልቻልክ ወላዋይ የሆነ አስሳስብ አንድ ጊዜ ኢሳያስን ትደግፋለህ አን ደግሞ በውያኔ ተጠቃ ብለህ ተደብቆ የነበረውን ዘረኛ አስተሳሰብ ገንፍሎ ተነሳብህ አኢትጵያን ሪቪው አልሽጥ ሲልህ አንተንና አስተሳብህ አፍትራሽና ደካማነቱን ሁሉም ስተረዳ ጨንቆህ በመሆኑ አርፈህ ተቀመጥ

  11. Elias there is no emergency psychiatric hospital around you?
    Please go there and take some rest bro
    Otherwise you will be die because of your fucking depression

  12. seme bante mewetatu rasu astelegne I really dont want to see ethiopian review again. you are a sick person or you are a lier.

  13. You are confused man! Stop confusing others with your sick mentality! Dr berhanu already said got no time to listen to tultulas
    we will keep on helping abegnoch ginbot 7

  14. ከሀዲው:ኤሊያስ:ክፍሌ:ይልማ:ገብረብ:ያኔ:ያመቱ:ሰው:ብለህ:አንተ:የጠራህው:የኤርትራው:መሪ:አልነበረም:ወይ:ያኔ:ኤርትራ:ሄደህ:ተገናኝተን:ነበር:ታስታውስ:ከሆነ:ቅርጫፍ:ጽፈት:ቤት:ልትከፍት:አስበህ:እንደነበር:ሰናይ:ገ/መድህን:ልትቀጥረው:አስበህ:እንደነበር:አዋርተህኝ:ነበር:ገንዘብ:ለማግኘት:ሞክረህ:ሳይሳካልህ:እንደቀረ:በኃላም:ለግንቦት7:እርዳታ:ሲያገኝ:አኩርፈህ:እንደሄድክ:እረሳህው:አንተ:ጥቅመኛ:አድር:ባይ:ባንዳ:ለግል:ጥቅም:ብለህ:ውሸት:ታወራለህ:ውሽት:ለአንተ:አዲስ:አይደለም:ያኔ:ለሸህ:አላህሙዴ:ልጅ:የጻፍከውን:የተከሰስክበትን:በውሽትህ:የደረሰብህን:እረሳህው:እባክህን:ይህን:ውሽትህ:ለኢትዮጵያ:ህዝብ:ይቅርታ:ጠይቅ:አንተ:ከአሁን:በኃላ:10 :አመት:አትኖርም:በሕይወት:እውነት: ተናግረህ:ብትኖር:ይሻላል:ክፍሊ:ሳይሆን:ቀዳዳው:ነው:ስምህ:አፍሰህ:ሙላው:አድር:ባይ:ባንዳ:ባንዳ:ነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*