ፓትርያርኩ: የረዳት ሊቀ ጳጳሱን የባንክ ሒሳብ የማንቀሳቀስ ሓላፊነት ያለቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ቀየሩ፤ ‹‹ተጠያቂነት እና መንፈሳዊ መከባበር የሌለበት የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኹኔታ አፋጣኝ መፍትሔ የሚያሻው ነው›› /ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ/

A.A Diosces Head Office

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት

  • አስተዳደሩን፣ የገንዘብ እና ንብረት እንቅስቃሴውን የመቆጣጠር ሕጋዊ ሓላፊነታቸው ተገድቧል
  • በዕቅድ ባልተያዙ ከፍተኛ ግዥዎች እና የወጪ ሰበቦች ምዝበራ ሊፈጸም እንደሚችል ተጠቁሟል
  • በቅ/ሲኖዶስ የተመደቡትን ረዳት ያጣው ሀ/ስብከቱ ከ50 ሚልዮን በላይ ተቀማጩ ለአደጋ ተጋልጧል

*        *        *

  • የሠራተኞች ደመወዝ እና አይቀሬ የኾኑትን ዕለታዊ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች እንዳይወጡ ፈቃደኛ ያልኾንኩበት እና ሥራዎች እንዲጓተቱ ያደረግኹበት ወቅት እስከ ዛሬ ድረስ የለም፡፡
  • በተመደቡት ሥራ አስኪያጅ እና በእኔ መካከል ያለው የሥራ ግንኙነት እና ሓላፊነት ከቃለ ዐዋዲው እና ከሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንጻር ታይቶ እና ተለይቶ በትክክል ባለመተግበሩ ሓላፊነቴን ለመወጣት በእጅጉ እቸገራለኹ፡፡
  • በሀገረ ስብከቱ የተረጋጋ እና ሰላማዊ የሥራ ግንኙነት እንዲኖር፤ ሓላፊነት፣ ተጠያቂነት እና መንፈሳዊ መከባበር ባለው ኹኔታ በሕጋዊ አሠራር ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የሥራ መመሪያ እንዲኖር ቅዱስነትዎ ትኩረት ይስጠው፡፡

/ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ/