ሰበር ዜና – አባላቱ በሀብታም እና ድኻ መከፈላቸውን የተቃወመው የሰሚት መድኃኔዓለም ሰንበት ት/ቤት በአለቃው ታሸገ፤ ‹‹ምርጫው ይለፍና አሳስራችኋል፤ ልክ አስገባችኋለኹ›› እያሉ ሲዝቱ ሰንብተዋል

Locked Finot Selam Sunday school gates banned

  • ርምጃው የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ፣ አመራሩ እንዲቀየር የጻፉትን ደብዳቤ መነሻ ያደረገ ነው
  • ለጥያቄአቸው ምላሽ ባለማግኘታቸው በፓትርያርኩ ላይ ቅሬታቸውን በመዝሙር ገልጸው ነበር
  • ከ200 በላይ አባላት የሚማሩበት አዳራሽና የሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት ቁልፎች ተሰብሮ ታሽግዋል
  • የደብሩ ስምንት አመራሮች ከመሳለም በቀር ወደ ደብሩ ገብተው እንዳይሰበሰቡ ተከልክለዋል

*       *       *

  • በካህናትና በምእመናን አንድነት መመራት ባለበት ደብር የአለቃው ዓምባገነንነት ሰፍኖበታል
  • ሰበካ ጉባኤ የለም፤ በአቋሜ አይስማሙም ያሏቸውን ብዙኃኑን የሰበካ ጉባኤ አባላት አግደዋል
  • ሦስት የሰንበት ት/ቤቱ አመራሮች የፖሊቲካ ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል ለቀናት ታስረው ነበር
  • ክሣቸው ተነሥቶ የሀብታም በሚል የተለየው ጉባኤ እንዲቀር የተሰጠው ትእዛዝ አልተፈጸመም
  • በደብሩ አቅራቢያ የሚገኘው የጎሮ ፖሊስ ጣቢያ አለቃው እንዳሻቸው የሚያዙበት ነው ተብሏል

*       *       *

  • በፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ንቅናቄው የተደናገጡ አማሳኞች የሐሰት አቤቱታ እያሰባሰቡ ነው
  • ‹‹ተሐድሶ የለም›› በሚል የሰንበት ት/ቤቶችን አመራሮች ለመከፋፈል እየተፍጨረጨሩ ነው
  • የማደራጃ መምሪያው ዋና ሓላፊና በሙስና የተጨማለቁ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎች ይተባበሯቸዋል
  • መላው የሰንበት ት/ቤቶች አባላት የአንድነቱን የወሳኝ ፍልሚያ ጥሪ በንቃት እየተጠባበቁ ነው