በዝምታ የተጀቦነው ምርጫ 2007 ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ ፀጥ እንዳለች ውላ አመሸች 
Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. May 24, 2015)፡- ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የተካሄደውና የተጠናቀቀው ምርጫ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት አራት ምርጫዎች እጅግ የቀዘቀዘ መሆኑ ታወቀ። ተቃዋሚዎች ፓርቲዎች በታዛቢነት የመደቧቸው ሰዎች ምርጫውን እንዳይታዘቡ ጫና እንደተደረገባቸው ብሎም እንደታሰሩባቸው ገልጠዋል፤ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ በምርጫ ከተሳተፉት ፓርቲዎች ምንም አይነት ቅሬታ እንዳልደረሰው ገልጧል።