እስከዛሬ ታይቶ የማያውቅ “አስካሪ” በመባል ይታወቁ ስለነበሩ ባንዳዎች የሚያሳይ ቪዲዮ
በ1888 ዓም በተደረገው የአድዋ ጦርነትና ከ40 ዓመት በኋላ በተደረገው የማይጨው ጦርነት ጊዜና ከዛም በኋላ በነበሩት አምስት የጠላት ዓመታት ወቅት በባንዳነትና በፍጹም ታማኝነት ለጣሊያን አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ከኤርትራ የመጡ ሰዎች “አስካሪ” ይባላሉ። አስካሪዎች በጭካኔያቸውና በክፋታቸው ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው ሲሆን ባህር ተሻግረው፣ ድንበር ሰብረው ከመጡት የጣሊያን ወታደሮች እጅግ በከፋ ሁኔታ በቀለም፣ በመልክ፣ በባሕል፣ በሃይማኖት፣ በስነልቦና በዘርና በሌሎችም ሁኔታዎች የሚመሳሰላቸውና የሚቀርባቸውን ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ መከራ አውርደውበታል። አስካሪዎች ከ4000 ዓመት በላይ ባለው የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ላይ ያወረዱት አሳርና ጭንቅ በቃላት ተነግሮ የሚያልቅና ከሌላ ጋር የሚወዳደር አይደለም። እነዚህ ሰዎች “ከለማበት የተጋባበት” እንደሚባለው ከጣሊያኖቹ ብሰው ከራሳቸው በመነጨ ክፋት በመገፋት ለጣሊያኖች ልቆ ለመታየትና ለመወደድ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰላማዊና እነሱን ምንም ያላደረጓቸው ኢትዮጵያዊያንን በማጅራታቸው አርደዋቸዋል።
የኢትዮጵያ አርበኞች በዱር በገደል ተዋድቀው የጣሊያንን ሰራዊት ድባቅ ሲያስገቡ አስካሪዎችም በወገናቸው ደም ሰክረው ሲቅበዘበዙ ተይዘው የእጃቸውን አግኝተዋል። መሬት የወደቀችው ሰንደቅ አላማችን ተመልሳ ከፍ ብላ ስትውለበለብ አስካሪዎችም እጅ እንዲነሱ ተደርገዋል። አጼ ሚኒሊክ ከአድዋ ጦርነት በኋላ አስካሪዎች ላይ ተመጣጣኝ ቅጣት የሰጡ ቢሆንም በማይጨው ጦርነትም ጊዜ አስካሪዎች ተመሳሳይ ግፍና በደል ኢትዮጵያዊያን ላይ አድርሰዋል። በጣሊያን ከ60 ዓመት ቅኝ ግዛት ከተያዙ በኋላ በርካታ የኤርትራ ክፍለ ሃገር ተወላጆች “ኢትዮጵያ ወይም ሞት” ብለው ወደ እናት አገራቸው ሲቀላቀሉ ጥይት የተተኮሰባቸውና የውንብድና ድርጊት የተፈጸመባቸው ከነዚሁ አስካሪዎች ርዝራዦች ማለትም ጀብሃዎች መሆኑ ይታወቃል። እነዚህም የኢትዮጵያን ደበኛ ጠላት የሆነውን ሻቢያን ወልደዋል። ስለአስካሪዎች ብዙ የሚታወቅ ቢሆንም ይህ ጥናታዊ ቪዲዮ ግን ጠቅለል ባለ መልኩ ማንነታቸውን በግልጽ ያሳያል። እራሱ አስረጅ የሆነውን ቪዲዮ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ።