የስብሃት ገብረእግዚአብሔር ዜና እረፍት
የእውቁ ደራሲ ና ጋዜጠኛ ስብሃት ገብረ እግዚአብሔር የቀበር ሰነ ሰርዓት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተፈፀመ ። በሰነ ፅሁፍ ባለሞያዎች የአጭር ለብ ወለድ አባት በመባል የሚደነቀው ሰብሃት በፈረንሳይ ና በዩናይትድ ሰስቴትስ ዩኒቨርስቲዎች ተምሯል ። ስብሃት በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት በዋና አዘጋጅነት ሰርቷል ። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሄቶች በአማርኛ ና በእንግሊዘኛ በየጊዜው የፃፈ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሃያሲ ነበር ። በቀበር ሰነ ስርአቱ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ታደሰ እንግዳው ዘረዘር ዘገባ አለው። ያዳምጡ