በምክክር መድረኩ ያልተጠበቀው የመንግሥት አቋም

በጉምሩክና በሎጂስቲክስ ችግሮች ዙርያ የግሉ ዘርፍ ያቀረበውን ጥናትና የመፍትሔ ሐሳቦች መንግሥት ያለማንገራገር ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ቃል ሲገባ፣ በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት የግል ዘርፉ ተሳትፎ ምን ይሁን የሚለውን ጥያቄ በጥናት አየዋለሁ ብሏል፡፡