የዜጎችን ክብር በመጠበቅ የአገር ክብር ይጠበቅ!

ሰሞኑን ወደ ኢሚግሬሽን ጽሕፈት ቤት አካባቢ ጎራ የሚል ሰው የሚያየው ለጥምቀት፣ ለደመራ ወይም ለኢድ የተሰበሰበ የሚመስል የሕዝብ ብዛትና መጨናነቅ እንጂ፣ ፓስፖርት ለማግኘት ተራ የሚጠብቅ ሕዝብ ነው ብሎ አይገምትም፡፡ ብዛቱ!