የኢትዮጵያ ህዝብ፣ … ከዚኽ ወዴት? ክ.16 (አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስራ ስድስት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

ኢዴኃኅ …

ሐ) ምሥረታ፦ የጉባዔው ተሳታፊዎች የአገሪቱን አጠቃላይ ሁኔታ እና ለለውጥ የቆሙ ህዝባዊ (ዴሞክራት) ኃይሎች ቀደም ሲል ትግላቸውን ለማስተባበር መሥርተዋቸው የነበሩ የጋራ መድረኮችን (ሕብረቶችን) ድክመቶች፣ ግድፈቶችና ጠንካራ ጎኖች በዝርዝር፣ በሰከነና በጥልቀት በመመርመር የጋራ ግንዛቤ ጨብጠዋል።