‹‹የኅብረቱ የምርጫ ውዝግብ በሻይ ኩባያ ውስጥ የተፈጠረ ማዕበል ዓይነት ነው››

ቡሉስ ፓል ሎሎ፣ በኢትዮጵያ የናይጄርያ አምባሳደር
ኢትዮጵያና ናይጄርያ በሕዝብ ቁጥር በአፍሪካ ቀዳሚነቱን የሚይዙ አገሮች ናቸው፡፡ሁለቱም አገሮች እምቅ ሀብትም እንዳላቸው ይነገራል፡፡የናይጄርያው ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ባለፈው ዓመት ወደ ሥልጣን በወጡ ጥቂት ወራት ውስጥ ነበር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና በአፍሪካ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ የመከሩት፡፡