የየካቲት 12 ሰማዕታት በአልማዝ ኢዮቤልዩ ሊዘከሩ ነው

በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በፋሺስት ኢጣሊያ ያለቁበት የየካቲት 12 ቀን ሰማዕታት 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የፊታችን ዓርብ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደሚዘከር የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም (ኢጥምተ) አስታወቀ፡፡