በገንዘብ ዕጦት ምክንያት የተገደበ ግደብ?
ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)
ከላይ ለዚህ ትችት የተሰጠው ርዕስ እንደሚያመለክተው በአንድ በኩል በገንዘብ እጦት ችግር ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ባለመቻሉ ምክንያት የተገደበ ወይም ደግሞ እንደ ጅብራ ተገትሮ የቀረ ግድብ የሚል ትርጉምን የሚይዝ ሲሆን፤ ሌላው ትርጉሙ ደግሞ ከፍተኛ በሆነ የገንዘብ እጦት ችግር ምክንያት የተመደበለትን ገንዘብ በማብቃቃት ለመስራት በማሰብ ደረጃቸውን ባልጠበቁ ግብዓቶች በመጠቀም ለርካሽ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል እንደምንም ተውገርግሮ የተሰራ ግድብ ብዙም ዘለቄታ ሳይኖረው በአንድ ወቅት አውዳሚ በሆነ መልኩ ተንዶና ተደርምሶ የህዝብ ሀብት እና ጉልበት መና ሆኖ ይቀራል የሚል ፍሬ ሀሳብን የያዘ ነው።