የእንጦጦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የማታ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ገለጹ
(በታምሩ ጽጌ)
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ባወጣው መመሪያ መሠረት ትምህርታቸውን በ10+3 ፕሮግራም መጀመራቸውንና ለሦስት ዓመታት ከተማሩ በኋላ ‹‹ሥልጠናችሁ በደረጃ 4 ነው›› የተባሉ የእንጦጦ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ የማታ ተማሪዎች፣ ከነሐሴ 7 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ቀን ትምህርት ማቆማቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡