እየተጠበቀ ያለው የናይጀሪያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት

በናይጀሪያ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ የተካሄደው ፕሬዚደንታዊ እና ምክር ቤታዊ ምርጫ ውጤት አሁንም ገና እየተጠበቀ ነው። ለፕሬዚደንታዊው ምርጫ በዕጩነት ከቀረቡት 14 ተወዳዳሪዎች መካከል ጠንካራው ፉክክር የተካሄደው በፕሬዚደንት ጉድላክ ጆናታን እና በተቃውሞው ቡድን መሪ መሀማዱ ቡሀሪ መካከል ነው።