ምርጫ ቦርድ ለቅንጅት የሰጠው የገንዘብ ድጐማ እያነጋገረ ነው
‹‹ሁለት መቀመጫ ያለው ቅንጅት የ40 ሰዎች ድጐማ ተሰጥቶታል›› አቶ ለገሰ ቢራቱ
‹‹ቅንጅት የገንዘብ ድጐማ የተሰጠው ፓርላማ ባለው ወንበር ልክ ነው›› አቶ አየለ ጫሚሶ
‹‹የምርጫ ቦርድ ሕጉን ጥሷል›› አቶ ተመስገን ዘውዴ
‹‹ድጐማውን የሰጠነው በመስፈርቱ መሠረት ነው›› አቶ ተስፋዬ መንገሻ
ራሳቸውን ከቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር አባልነት ያገለሉት የቀድሞው የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለገሰ ቢራቱ፣ በ2002 ብሔራዊ ክልላዊ ምርጫ በፓርላማ ሁለት መቀመጫ ብቻ የነበረው ቅንጅት፣ 40 መቀመጫ እንዳለው ተደርጐ በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ 174 ሺሕ ብር የገንዘብ ድጐማ የሰጠው መሆኑን አስታወቁ፡፡