የስብሰባ ጥሪ በቦስተንና አከባቢው ለምትኖሩ ሁሉ
የጋራ ዓላማዎች ምንድናቸው?
እውነት የጋራ ግቦች አሉን?
ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ፍትሕ ነጻነት እኩልነት ብልጽግና ሁሉም ሰው እመኛለሁ ይላል። ይኼንኑም እውን ለማድረግ በተናጠልና ተበታትኖ ከመልፋት በጋራ ተደራጅቶ የጋራ ዓላማ ሰንቆ መታገል አማራጭ የለውም እያለ ደቂቁም ግዙፍም የፓለቲካ ድርጅት ይሰብካል። ታዲያ ልምዳችን የሚመሰክረው ይኼንኑ ነው? ለመሆኑ የጋራ ዓላማ ምንድ ነው? እንዴትስ ይገነባል? የጋራ ዓላማ ባለቤቶችስ እነማን ናቸው? መጋራትና መቻቻልስ ምን ዓይነት ቦታ አላቸው በሚሉ ጥያቄዎችና በተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ የጠረጴዛ ውይይት ይደረጋሉ። ለሁሉም ክፍት ነው፡ ይምጡና ውይይቱን ያዳብሩ!
ከማክበር ሰላምታ ጋር
አዘጋጆች
ቀን ፡ እሁድ ፌብርዋሪ 26 (February 26, 2012)
ሰዓት፡ 3 PM- 6 PM
ቦታ፡ 21 ዋልደን ስኼር (21 Walden Square)
ኬምብሪጅ (Cambridge, MA 02140)