ኢትዮጵያ – የቅጂ መብቶች እና የቅጂ ወንጀሎች! (ሊያነቡት የሚገባ)
ፕሮ/ር አለማየሁ ገብረማሪያም
ትርጉም፦ ኢትዮጵያ ዛሬ (ኢዛዝክ)
የአእምሮ ውጤቶች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች
አንድ ሰው የሌላን ሰው ቤት ቢያቃጥል ወይንም ጉዳት ቢያደርስ በየትኛውም ሀገር ውስጥ ባሉ ህግጋት ንብረት በማውደም ወንጀል ተጠያቂ ይሆናል። አንድ መጸሀፍ መደብር ገብቶ በሺህዎች የሚቆጠሩ መጻህፍትን በመዝረፍ ለመንገደኛ ሁሉ የሚያድል ቢኖር ይህም በንብረት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሆኖ ይቆጠራል። የመጽሀፍ ቅጂ መብትን (ኮፒ ራይት) ጥሶ መጽሀፉንም በመቃኛ ቃኝቶ (እስካን) በዘመኑ ቴክኒዮሎጂ በድረ ገጽ ላይ የሚያወጣ ምን ይባላል? ይህስ አስከፊ የወንጀል ተግባር አይሆንምን? ህሊና ቢስ እኩይ ምግባርስ አያስብልምን?