የአፍሪካ አባት አጼ ኃ/ስላሴ እንጂ ክዋሜ ንክሩማ አይደሉም!
ያዕቆብ ኃይለ ማርያም (ዶ/ር)
አፍሪቃውያን በአረቦች እየተፈነገሉ ለነጮች ተሽጠው ባህር ሲሻገሩ ንብረታቸውም ወደ አውሮፓና አሜሪካ ሲጋዝ ብዙ ምዕተ ዓመታት እንዳስቆጠሩና ከሃያ ሚልዮን ያላነሱ አፍሪቃውያን በዓለም ዙሪያ እንደተበተኑ ታሪክ ዘግቦአል። እነዚህኑ አፍሪቃውያን ባህር ማዶ ለማሸጋገር፣ በመርከብ ውስጥ ከታጨቁበት ቀን አንስቶ የተለያዩ ግብታዊ አመጽ ቢያካሄዱም ወደ ካሬ ቢያን የተጋዙት ባሮች እንዲሁም ዘግይተው ነፃ የወጡት ተሳብስበው በ18ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ መላው ጥቁር አቀፍ የነፃነት እንቅስቃሴ (PANAFRICANISM) ጀመሩ።