የቴሌ ተከሳሾች በአንድ የክስ መዝገብ በነፃ ተሰናበቱ

በታምሩ ጽጌ

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በግንቦት ወር 2000 ዓ.ም. በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በአራት የክስ መዝገብ ክስ መስርቶባቸው የነበሩት፣ የቀድሞው የኢትዮጽያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ብሩን ጨምሮ 14 ተከሳሾች በአንድ የክስ መዝገብ ከትናንት በስቲያ በዋለ ችሎት በነፃ ተሰናበቱ፡፡