አርቲስት ሐመልማል አባተ ፍትሕ በማጣቷ ነጠላ ዜማ እንደምትለቅ አስታወቀች
በታምሩ ጽጌ
‹‹ቀበሌ ስሄድ የሚመለከተው ክፍለ ከተማውን ነው ይሉኛል፤ ክፍለ ከተማ ስሄድ ደግሞ እኛን አይመለከተንም፤ የሚመለከተው አስተዳደሩን ነው ይሉኛል፤ አስተዳደሩ ዘንድ ስሄድ ደግሞ ይኼማ የክፍለ ከተማው ሥራ ነው ይሉኛል፤›› ያለችው አርቲስት ሐመልማል አባተ፣ ለመንግሥትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕ ማጣቷን ለማሳወቅ አንድ ነጠላ ዜማ በቅርቡ እንደምትለቅ ለሪፖርተር አስታወቀች፡፡