ግብፅ 29 ኢትዮጵያንን ዲፖርት አደረገች
ኢትዮ እማማ)
ከሳምንታት በፊት ወደ እስራኤል ለመግባት ያሰቡ 29 ኢትዮጵያንን ድንበሯ ላይ ይዛ የነበረችው ግብፅ ዲፖርት ማድረጓን የኩዌት ዜና አገልግሎት ኩና (KUNA) ከካይሮ አስታወቀ።
ዜና አገልግሎቱ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ኢትዮጵያውያኖቹ በሶስት ምድብ ተከፍለው ከሲናይ በረሀ ወደ ካይሮ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መወሰዳቸውን ገልጿል።
የመጀመሪያዎቹ 18 ሲሆኑ ፤ሁለተኛዎቹ ሰባት፤ የመጨረሻዎቹ አራት እንደሆኑና ዓርብ እለት ካይሮ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሱ በኋላ ወደ ሀገራቸው መላካቸውን ዘግቧል።
በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወደ እስራኤል ለመግባት ሲሞክሩ በግብፅ ወታደሮች ከግድያ አንስቶ በሲናይ እስር ቤቷ ውስጥ የተለያዩ አሰቃቂ ድርጊቶችን በእስረኞቹ ላይ እንደምትፈፅምባቸው በተለያዩ የዜና አውታሮች ከዚህ በፊት መገለፁ ይታወሳል።