ብሔራዊ ባንክ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በማንኛውም ባንክ ውስጥ እንዳይሠሩ አገደ
– አቶ ኤርሚያስ ውሳኔውን በመቃወም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤት ብለዋል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዘመን ባንክ ዋና አደራጅና የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ ኤርሚያስ አልመጋን በዘመን ባንክ ቦርድ ውስጥ እንዳይሠሩ ከዚህ ቀደም የጣለውን እገዳ በማፅናት፣ ከዚህ በኋላ በየትኛውም ባንክ ውስጥ እንዳይሠሩ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡