መስቀልኛ ? ”የጐንቻው!

ሳር ቅጠል፤ ግማዱ፤ ተፍተለተለና፤
ሽምቀቅ ማተብ ሆነ፤እምነቱ፤ቀረና፤
በላይን ሰቀሉት፤የላቀውን ጀግና፤
ከጠላት ባዳናት፤በአገሩ፤መዲና፤
በግፍ፤ተሰቀለ፤‘እሙን ዋስ’፤ጠፋና፤
ማነቆ አደባባይ፤የትውልድ ገመና፤
ስቅላት ውለታው፤እርግምት ሆነና፤
ብርክ መዳህ ጀመርን ነፃነት፤ልመና፤
ያውም ከባዕድ አገር ተሰፍሮ፤በቁና፤
በላይ እምቢ ብሎ አኛ እጅ ሰጠንና፤
እንጠፋፋለን ‘በአሳር’፤ እንደገና፤
ይድረስ፤ለአገር ዳኛው፤‘ሕዝቡ በደፈና’፤
ዛሬም ‘ክህደታችን’፤አልተፋቀምና፤
ጀግኖች፤እየገብርን፤‘ቃሊቲ፤ ቀጠና’፤
ስንት ‘በላይ’ ሰቅለን እንሰይም ጐዳና፤
ሰንሰለት እንስበር ጸንተን እንቁምና።

በዘመነ ንጉሥ፤‘በግርማሜ’፤ሞት፤
አገር ሳይቆጣ፤ሳይተጋ፤ወጣት፤
በዘመነ ‘ደርግም’፤በ‘ሺህዎቹ፤እልቂት’፤
ጥቂቶች፤ሲተጉ፤’መንጋው’ ሲራኮት፤
የባሰ፤ደንቀራ፤ተጋረጠባት፤
‘እናት’ በጓዳዋ፤የልጅ ቁርኝት፤
ዘመነ፤ወያኔ፤መከራ፤ግዞት፤
አገር-ሕዝብ፤የሚያሥር፤በዘር ሰንሰለት።

ሕዝብ የሚያስጨርስ ነፍሰ-በላ፤ዳኛ፤
ለምን አይጠየቅ፤በአገር አደባባይ፤ችሎት ‘መስቀልኛ’፤
ሁነኛ ሰው ጠፍቶ፤ጠበቃ፤የሚሆን፤ አዋቂ ቁርጠኛ፤
‘እድሜ፤ልክ’ እሥራት፤ ይፈረዳል ‘በእኛ’፤
ይድረስ ለአገር ሸንጐ፤ይድረስ ለአገር ዳኛ፤
ለምን ፍትህ አትሰጥ፤ይግባኝ የማይሸረው፤በአሳሪና እስረኛ፤
ብይን አስቆጭተህ፤እጥር ምጥን ያለ፤‘ሰውኛ-አገርኛ’፤
አትደግስም ወይ፤በቀናት፤በወራት፤ወያኔን መሸኛ።
እንባ ባዘነበው፤ደም በቋጠረው፤ሃይቅ፤
በፍርሃት ማዕበል፤አገር ሲጥለቀለቅ፤
በክህደቱ መንደር፤ጐርፉ፤ሲጨናነቅ፤
በወያኔ አዞዎች፤ሰው በቁም ፤ሲቦጨቅ፤
ገመና እሚሸፍን፤ሱሪ፤የሚያስታጥቅ፤
በአገር ጀግና ነጥፎ፤ወንዙ፤ምንጩ፤ሲደርቅ፤
ጓዳ እሚያወላዳ፤ቀሚስም እሚያጠልቅ፤
በአዘቦት፤በጥምቀት፤አድባር ሲሸማቀቅ፤
ቅርጣን የተረፉ፤ቃል፤የጠበቁ፤ሃቅ፤
‘የቀኑን ጭለማ’፤በብዕር በማድመቅ፤
እውነት ትንፍሽ ያሉ፤ዓለማችን እንዲያውቅ፤
‘ከመሸበት ሊያድሩ’፤‘ጮራ እሲኪፈነጥቅ’፤
የ’ግርማሜን’ መንፈስ፤የበላይን ሰንደቅ፤
እንቁ የአበሻ፤ልጆች፤የትውልድ ፈርጥ ወርቅ፤
ስማቸው፤አርማቸው፤በአለም የሚደነቅ፤
ማተብ ይሁን አልቦ ካቴናቸው፤ይውለቅ፤
ይድረስ ለአገር ዳኛው፤አፎት፤እንዲታጠቅ፤
አሳሪው ይታሰር፤ክህደቱ፤ይሽምቀቅ።

በአኬልዳም ሽብር፤የተፈረጁት፤
‘ጥፋት’ ባጋለጡ፤እስር ስቅላት፤
አንዷለም፤እሥክንድር፤ጀግናዋ ርዕዮት፤
ዘመኑ፤በቀለ፤ናትናዔል፤አሳምን፤ደግሞም፤ውብሸት፤
ከሺህ ተቆራኝተው፤ስለ ሕዝብ፤ስለ አገር የተሳሰሩት፤
ለዓለም መቀጣጫ፤ንብረት-ነፍስ፤አራጣ፤የሚገብሩት፤
መጋጥ በለመደው፤ ያረጀ ያፈጀ ነቅዝ፤ስርዓት፤
ይድረስ የአገር ዳኛ፤ዋስም ጠበቃ ሁን፤ውጣና ‘ታገት’፤
አበሳችን ይሻር፤ሰይም አደባባይ፤የእምነት የምህረት፤
ሕዝብ ሸንጐ፤ጠርቶ፤የብይን ችሎት፤
ይፍረድ፤ የአገር ዳኛ፤በቀን በወራት፤
ታሳሪ፤አሳሪውን፤እንዲጠይቁት፤
በአገር ‘መስቀልኛ’፤እንዲያፋጥጡት

በእስር፤ለሚንገላቱት ወገኖቻችን መጽናኛ ትሁንልኝ፤
የጐንቻው!
[email protected]