በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚጠቀሙ ናይጄራውያን አውሮፕላን ውስጥ እየሞቱ ነው
ኢትዮ እማማ
በአንድ ሣምንት ብቻ ሁለት ናይጄራውያን ሞተዋል።ባለፈው እሁድሣምንት ከአዲስ አበባ ወደ አቡጃ ሲበር በነበረ አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ዘይኔባ ሱሊማን የተባሉ የ62 ዓመት አዛውንት በመሞታቸው አውሮፕላኑ ዳግም ለማረፍ ከተገደደ በኋላ በሌላ አውሮፕላን አስክሬኑ እንዲሄድ ተደርጓል።
አየር መንገዱ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ከገዛቸው አምስት ቦይንግ 777-200ኤልአር አውሮፕላኖች መካከል ሁለተኛው አውሮፕላን
የሴትየዋ ባለቤት አላሀጂ ሱሊማን ለናይጄሪያ የዜና ወኪል በሰጡት መግለጫ በሕንድ ኒውደሊ የካንሰር ሕክምና አድርገው ወደ ሀገራቸው ናይጄሪያ እየተመለሱ እንደነበር ገልፀው ሌላ አውሮፕላን ለመቀየር አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ለአንድ ሰዓት ያህል ከቆዩ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አውሮፕላን በመያዝ ወደ አቡጃ በመመለስ ላይ እያሉ አውሮፕላኑ ከተነሳ ከ1 ሰዓት ከ30 በኋላ ባለቤታቸው በመሞታቸው አውሮፕላኑ እንደገና ለማረፍ መገደዱን ገልፀዋል።የሚስታቸው ሞት ከበሽታው ጋር የተያያዘና የእግዚያብሔር ጥሪ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፈው ሣምንት በተያያዘ ሁኔታ ከአቡጃ ወደ ኒውደሊ ሲበር በነበረ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ሌላ የናይጄሪያ መንገደኛ መሞቱ ታውቋል።
በርካታ ናይጄራውያን ለአሽሽ ንግድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን ስለሚጠቀሙ አሽሹን በላስቲክና በኮንዶም አድርገው ወደ ሆዳቸው በማስገባት ለማሳለፍ በሚሞክሩበት ወቅት አሽሹ የተቋጠረበት ላስቲኩ ወይንም ኮንደሙ ስለሚፈነዳ በርካታ ናይጄራውያን ለሞት እንደሚዳረጉ ታውቋል።