“ሸቦ ግቢ እንገናኝ” ሊቀር ነው (ግርማ ደገፋ ገዳ)

ሆላንዶች አበባ ይወዳሉ። ወንጂ ውስጥ ያላመጡት አበባ የለም። በተለይ ሽቦ ግቢ ውስጥ ከሆላንድ የመጡ አበቦችና ዛፎች በብዛት ይታያሉ። ቤታቸውና ቢሯቸው ዓይን በሚማርኩ ልዩ ልዩ አበቦች የተከበበ ነው። ሽቦ ግቢ ያደጉ ያካባቢያችን ልጆች፣ ማለዳ ከእንቅልፋቸው ተነስተውና መስኮታቸውን ከፈት አድርገው፣ እነዚያን ውብ አበባዎች እየተመለክቱ፤ “Today is a beautiful day” ይላሉ ብለን እናስባለን። (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)