በሕፃናት ላይ ፆታዊ ጥቃት ያደረሰው የ16 ዓመት ወጣት በ25 ዓመት እሥራት ተቀጣ

በሚኪያስ ሰብስቤ

በስድስት ሕፃናት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሟል በሚል በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመስርቶበት ከአንድ ሳምንት በፊት በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ሰባተኛ ወንጀል ችሎት ጥፋተኝነቱ የተረጋገጠበት የ16 ዓመት ወጣት፣ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ታህሳስ 7 ቀን 2003 ዓ.ም. የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ፡፡